በዙሪክ የዳይመንድ ሊግ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቶች የወርቅ ሜዳሊያ ያገኛሉ ተብሎ ይገመታል

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በ14ኛዉ ዙር የዳይመንድ ሊግ ዉድድር ዛሬ ምሽት ሲካሄድ በወንዶች 3 ሺህ ሜትር አራት ኢትዮጵያውያን ተፎካካሪዎች ወደ ሜዳ ይገባሉ።

በዚህ ርቀት በሶስት የተለያዩ ከተሞች የዳይመንድ ሊግ ተሳትፎ ያደረገዉ ቢኒያም መሀሪ ቀዳሚዉ ተጠባቂ አትሌት ነዉ። ከቢኒያም በተጨማሪ በ3 ሺህ ሜትር ሶስት ጊዜ እንዲሁም በ2 ማይል አንድ ጊዜ የተወዳደረዉ መዝገቡ ስሜ፣ አብዱሰላም ወርቁ እና አብዲሳ ፈይሳ በውድድሩ ላይ የሚሳተፉ ይሆናል።

በሴቶች ዘርፍ በ3 ሺህ ሜትር የመሰናክል ሩጫ አለምናት ዋለ ሀገሯን ወክላ በብቸኝነት ትወዳደራለች። አትሌቷ በበጀት አመቱ ለአምስተኛ ጊዜ በርቀቱ የሚኖራት ተሳትፎ ሲሆን ባለፈዉ ግንቦት ወር በቻይና አምስተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ የዓመቱ ከፍተኛ ስኬቷ ነዉ።

በሌላ በኩል በ800 ሜትር ሰይዳ ፀሀዬ ከአውሮፓውያን አትሌቶች ጋር ብርቱ ፉክክር ታደርጋለች።

በዚህ የዳይመንድ ሊግ ውድድር ከኢትዮጵያውያን በተጨማሪ የኬንያ እና የኡጋንዳ አትሌቶች ለድል እንደሚበቁ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷቸዋል።

#DiamondLeague #athletics #sports #ethiopianathletes #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: