አሜሪካ በትግራይ ጉዳይ ላይ ስምምነት እንዲደረግ ጠየቀች፤ ህወሓት ከአፍሪካ ህብረት ውይይት በፊት ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀመጠ​በ…

- Advertisement -
Sidebar AD
አሜሪካ በትግራይ ጉዳይ ላይ ስምምነት እንዲደረግ ጠየቀች፤ ህወሓት ከአፍሪካ ህብረት ውይይት በፊት ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀመጠ
​በአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ የመቀሌ ጉብኝት ማብቂያ ላይ አሜሪካ በኢትዮጵያ መንግስት እና በትግራይ አመራሮች መካከል እርቅ እንዲወርድ እና ስምምነት ላይ እንዲደረስ ጥሪ አቀረበች።
​በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ እና የአፍሪካ ህብረት የዩኤስ ሚሲዮን ጉዳይ ፈጻሚ ዎልተር ፓርስ በጋራ ባወጡት መግለጫ፣ የኦባሳንጆ ጥረት እንዳበረታታቸው ገልጸው  ውይይቱን እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
አሜሪካ ቀዳሚ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት እና ተፈናቃዮችን ወደ ቀደመ ቀያቸው በሰላም የመመለሱ ሂደት እንደሆነ አስታውቃለች።
​በሌላ በኩል ህወሓት በሰጠው ምላሽ በቅርቡ ከመቀሌው ውይይት ከአዲስ አበባ በኩል የመጣ “አዲስ ሃሳብ ወይም የእድገት ማሳያ የለም” ሲል ገልጿል።
ድርጅቱ ከመደበኛ ድርድር በፊት መፈታት ያለባቸውን በርካታ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጧል።
​ህወሓት ካቀረቧቸው ቅድመ ሁኔታዎች መካከል፡
👉​ወታደራዊ ከበባ እንዲያበቃ እና የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንዲነሳ፣
👉አከራካሪ ቦታዎች  ነፃ ወጥተው ተፈናቃዮች እንዲመለሱ፣
👉​የህወሓት ህጋዊ እና ፖለቲካዊ ህልውና ሙሉ በሙሉ እንዲመለስ የሚሉ ይገኙበታል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: