ኢጅፕት ኤር ከባርሴሎና ጋር ታሪካዊ ስምምነት አደረገ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ኢጅፕት ኤር ከባርሴሎና ጋር የ3 ዓመት የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ተፈራረመ።

የግብፁ ብሔራዊ አየር መንገድ ኢጂፕት ኤር ከስፔኑ ክለብ ባርሴሎና ጋር እስከ 2028/29 የውድድር ዘመን መጨረሻ ድረስ የሚዘልቅ የሶስት ዓመት የዓለም አቀፍ አጋርነት ስምምነት ተፈራርሟል።

በስምምነቱ መሠረት አየር መንገዱ የባርሴሎና የወንዶች እግር ኳስ የባስክቴቦል ቅርጫት ኳስ እና የእጅ ኳስ ቡድኖች ዋና የበረራ አጋር ሆኖ ያገለግላል።

የኢጅፕት ኤር መለያ ሎጎ በባርሴሎና ማሊያ ፊት ለፊት ላይ የሚያርፍ ይሆናል።

ኢጅፕት ኤር የዓለም አቀፍ በረራዎቹን ተደራሽነት ለማስፋት እና የአየር መንገድ ስሙን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ያለመ ነው ብሏል።

ባርሴሎና በበኩሉ በመካከለኛው ምስራቅ እና በአፍሪካ ያለውን የደጋፊዎች ቁጥር እና የንግድ እንቅስቃሴው የበለጠ ለማጠናከር ያለመ ስምምነት ነው ያደረገው ተብሏል።

ይህ ስምምነት ባርሴሎና ከኳታር አየር መንገድ ጋር የነበረው ውል ካጠናቀቀ በኋላ ከኢጂፕት ኤር ጋር ያደረገው የመጀመሪያው ትልቅ የአጋርነት ስምምነት ነው።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#Egypt #Barcelona #football
#Sponsorship #agreement
#Airlines #EgyptAir


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1