460 የሚጠጉ ሰዎችን ሕይወት የታደገው የድልድዩ ጠባቂ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በቻይና የናንጂንግ ያንግትዜ ወንዝ ድልድይ በዓለም ላይ በርካታ ሰዎች ሕይወታቸውን ለማጥፋት የሚመርጡት አስፈሪ ሥፍራ በመባል ይታወቃል።

ነገር ግን ላለፉት 21 ዓመታት በዚህ ድልድይ ላይ አንድ ያልተለመደ ተአምር ሲፈጸም ቆይቷል።

በድልድዩ እራሳቸውን ለማጥፋት የመጡ 469 ሰዎችን በቼን ሲ እርዳታ ከሞት ተርፈዋል።

ቼን በወጣትነቱ በከባድ ድህነትና መከራ ያሳለፈው ሲሆን ከፈረንጆቹ 2003 ጀምሮ ቅዳሜና እሁድ ሙሉ በሙሉ ድልድዩ ላይ በመዘዋወር ወደዚህ ድልይ የሚመጡትን ሰዎች መጠበቅ ጀመረ።

ቼን በሞተር ብስክሌቱና በእግሩ ድልድዩን እያሰሰ የተስፋ መቁረጥ ምልክት የሚያሳይና ተክዞ የሚሄድ ማንኛውንም ሰው በነፃነት ቀርቦ ያናግራል።

የሥነ-ልቦና ትምህርት ሳይማር በራሱ የሕይወት ልምድና ደግነት ብቻ የሰዎችን ጭንቀት ይረዳል።

አንዳንዶቹን በንግግር ሌሎቹን ደግሞ በጉልበቱ እየጎተተ ከሞት አትርፏቸዋል።

የሌሎችን ከባድ ሕመም እና የተወሰኑ ማዳን ያልቻላቸውን ሰዎች ትዝታ በሕልሙ እያየ ለዓመታት ትልቅ የሥነ-ልቦና ጫና አስተናግዷል።

ቼን ሲ እንደሚለው አንዳንዴ ሰዎችን ከከፋ አደጋ ለማዳን ሳይንሳዊ እውቀት ሳይሆን በቦታው ተገኝቶ ሰብአዊ ርህራሄ ማሳየት ብቻ በቂ መሆኑን ተናግሯል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#China #bridge #suicides
#NanjingYangtzeRiver
#psychological #pressure


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: