የአፍሪካን አቪዬሽን ዘርፍ ልህቀት ጋናም ተቀላቀለች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ጋና በአክራ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከ2,000 በላይ የተሽከርካሪ ማቆሚያ ቦታዎችን የሚያካትት ግዙፍ አዲስ የኤርፖርት ማዕከል ግንባታ ለመጀመር ተዘጋጅታለች።

በፕሬዚዳንት ጆን ድራማኒ ማሃማ ይፋዊ የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጥ የሚጀመረው ይህ ባለ ሰባት ፎቅ ዘመናዊ ፕሮጀክት የሀገሪቱን ዋና የአቪዬሽን ማዕከል በከፍተኛ ደረጃ የሚያስፋፋና የሚያዘምን እንደሆነ ተገልጿል።

​ይህ ግዙፍ ግንባታ የተጓዦችን ምቾት ከማሳደግ ባሻገር ሁለት ዘመናዊ ሆቴሎችን፣ የገበያ ማዕከል፣ የምግብ አዳራሽ፣ ለችርቻሮ ንግድና ለቢሮ የሚሆኑ ክፍሎችን እንዲሁም ልዩ የሰማይ ላይ እይታ ማረፊያዎችን (sky lounge & sky observatory) በውስጡ ያካተተ ይሆናል።

በ24 ወራት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ፕሮጀክት፣ አክራ ዓለም አቀፍ አየር መንገድን በክልሉ ተወዳዳሪና ዘመናዊ የአቪዬሽን ማዕከል ለማድረግ ያለመ ነው።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2