የስፖርት ቤተሰቡን እና የሕዝቡን ፍላጎት ተረድቶ፣ እንዲህ አይነት ትልልቅ እና በጉጉት የሚጠበቁ የቦክስ እና የነጥብ ውድድሮችን (Adwa Fight Night) በነጻ እስከ መኖሪያ ቤት ድረስ ማድረሱ የሚደነቅ ነው። የቲኬት ዋጋ ውድነት በብዙዎች ላይ ይፈጥር የነበረውን መሰናክል በመቅረፍ ለብዙኃኑ የስፖርት አፍቃሪ ትልቅ እፎይታ እና ደስታን ሰጥቷል።
የቀረጻ፣ የድምፅ እና የዳይሬክቲንግ ጥራትን በተመለከተ ደግሞ እንደሚታወቀው እንዲህ አይነት የቀጥታ ስርጭት (Live Stream) ስራዎች በሄዱ ቁጥር እየዳበሩ እና እየተሻሻሉ የሚሄዱ ናቸው። በሂደት ደግሞ ልምድ እየቀሰሙ አሰራራቸውን ይበልጥ እንደሚያዘምኑና ለወደፊቱ የተሻለ ጥራት ያለው ስርጭት እንደሚያቀርቡልን አንጠራጠርም።
መልካም ስራን ማመስገን እና ማበረታታት ለቀጣይ የተሻለ ስራ ትልቅ አቅም ስለሚሆን፣ ምስጋናው እና ድጋፉ ይገባቸዋል!
Source: FastMereja









No comments yet.