የሁሊያን አልቫሬዝ የመጨረሻው ቀን

- Advertisement -
Sidebar AD

ወደ አርሰናል ወይስ በይቅርታ በአትሌቲኮ ይቆያል?

በሁሊያን አልቫሬዝ የዝውውር ጉዳይ ላይ አትሌቲኮ ማድሪድ እና አርሰናል ያስቀመጡት የጊዜ ገደብ ዛሬ የሚያበቃ ሲሆን፣ አርጀንቲናዊው አጥቂ የአርሰናልን ጥያቄ ተቀብሎ ወደ ለንደን ማመራት ወይም ለአትሌቲኮ ማድሪድ ይቅርታ ጠይቆ በክለቡ መቆየት እንዳለበት ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት አልቫሬዝ ለአትሌቲኮ ማድሪድ፣ ለአሰልጣኞች፣ ለቡድን አጋሮቹ እና ለደጋፊዎች ይቅርታ የመጠየቅ እድሉ እጅግ አነስተኛ እንደሆነ ይገመታል።

ተጫዋቹ ማክሰኞ ዕለት የተመከረውን ልምምድ በማቃለሉ አትሌቲኮ ማድሪድ ደስተኛ ያልነበረ ቢሆንም፣ በወቅቱ ነገሩን በዝምታ አልፎታል።

ነገር ግን በማክሰኞ ምሽት የታመመ መሆኑን ቤተሰቦቹ ለክለቡ ካሳወቁ በኋላ፣ ተጫዋቹ የረቡዕ፣ የሐሙስ እና የዓርብ ልምምዶችን ሙሉ በሙሉ አቃጥሏል።

በተለይም የረቡዕ ዕለት ልምምድ መቅረቱ ሁኔታውን ሙሉ በሙሉ የቀየረው ሲሆን፣ አልቫሬዝ ለሚላኩለት መልእክቶች ምላሽ በመከልከሉ የክለቡ ከፍተኛ አመራር ማቴው አለማኒ ወደ ቤቱ በአካል በመሄድ መፍትሔ ለመፈለግ ተገዷል።

ይህንን ተከተሎም አልቫሬዝ ከቤተሰቦቹ፣ ከተወካዮቹ እና ከህግ አማካሪዎቹ ጋር ረጅም ስብሰባ ያደረገ ሲሆን፣ የዝውውር አማራጮቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠበቡ መምጣታቸው ተጠቅሷል።


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: