#Ethiopia | የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከሮይተርስ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ባካሄደው ውይይት ላለፉት ስድስት ወራት ታግደው የነበሩ የሦስት ቋሚ የዜና ወኪሎቹን የዘገባ ፈቃድ ማደሱን አስታወቀ።
የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኃይማኖት ዘለቀ ከዓለም አቀፉ የዜና ተቋም ኤክስክዩቲቭ ኤዲተር ኒክ ታተር እና የአፍሪካ ኤዲተር ሲልቪያ አሎይሲ ጋር በተወያዩበት ወቅት ተቋሙ ባለፉት ሰባት ወራት ያሰራጫቸው አንዳንዶቹ ዘገባዎች የሀገሪቱን ሕግ፣ የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ እና ብሔራዊ ጥቅም የሚጻረሩ እንዲሁም ሙያዊ ሥነ-ምግባርን ያልጠበቁ እንደነበሩ የክትትል ውጤቶችን በማስደገፍ አስረድተዋል።
ዋና ዳይሬክቷ አክለውም የሮይተርስ ዘገባዎች ሚዛናዊነት፣ ትክክለኝነትና ተአማኒነት ጎድሏቸው ወደ አንድ ወገን ያደሉ እንደነበሩ በመጠቆም ለተፈጠሩት የሕግና የሙያ ጥሰቶች የዜና ተቋሙ አስፈላጊውን እርማትና ማስተካከያ ለማድረግ መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል።
የሮይተርስ ኃላፊዎች በበኩላቸው ተቋማቸው ገለልተኛ መሆኑን በመግለጽ ዘገባዎችን ከአድልዎ በጸዳ መልኩ ለመሥራት ጥብቅ መመሪያዎችን እንደሚከተል አስረድተዋል።
አልፎ አልፎ ለተከሰቱ ስህተቶች ይቅርታ በመጠየቅ ማስተካከያ እንደሚያደርጉና የኢትዮጵያን ሕግ፣ ባህላዊ እሴቶችና ብሔራዊ ጥቅም አክብረው ለመሥራት እንደሚጉ ቁርጠኝነታቸውን አረጋግጠዋል።
በውይይቱ ማጠቃለያ ላይም ታግዶ የቆየው የሮይተርስ ዘጋቢዎች ፈቃድ እንዲታደስ የተደረገ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ ለጋዜጠኞቹ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ባለሥልጣኑ ጥሪ አቅርቧል።
#reuters #ethiopiamedia #journalism #pressfreedom #ema
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen









No comments yet.