የዉሃ መስመር በመሰበሩ በአንዳንድ አከባቢዎች ላይ የዉሃ አቅርቦት ተቋረጠ
በአዲስ አበባ ከተማ በባለ 800 ሚሊ ሜትር ዲያሜትር ስፋት ያለዉ የዉሃ ግፊት መስጫ መስመር ላይ ስብራት ማጋጠሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታውቋል ።
የባለስልጣኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ሰርካለም ጌታቸዉ ከብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸዉ ቆይታ እንደገለፁት ከገላን የጋራ መኖሪያ ቤት አከባቢ የሚገኝ እና በተለምዶ አቃቂ ክፍለ ከተማ 3ሀ ተብሎ ከሚጠራዉ የግፊት መስጫ ጣቢያ ወደ ሀና ማሪያም የግፊት መስጫ ጣቢያ የሚወስደው ባለ 800 ሚሊ ሜትር ከባድ የግፊት መስጫ መስመር ግንባታ በሚገነቡ ባለሀብቶች ምክንያት ተሰብሯል ።
በዚህም የተነሳ ሀና ሰፈራ፣ሀና ማሪያም፣ አዲስ አበባ እና ኦሮሚያ የጋራ መኖሪያ ቤቶች፣ ሀና ፉሪ፣ ላፍቶ፣ ጀሞ አንድ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እና አካባቢው እንዲሁም ቫርኔሮ እና ለቡ ሙዚቃ ቤት አካባቢ ውሃ ማሰራጨት እንዳልተቻለ ተገልጿል ።
ባለስልጣኑ መስመሩን ለመጠገን ሙሉ የከባድ መስመር ባለሙያዎችን ማሰማራቱን ገልጿል ። መስመሩን ተጠግኖ ወደ መደበኛ ስርጭት እስኪመለስ ድረስ ደንበኞች በትእግስት እንዲጠባበቁ መልዕክቱን አስተላልፏል ።
@Seledadotio

- Advertisement -

No comments yet.