#Ethiopia | ቀደም ሲል የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን በነፃ ወደ አየር ለማዋል ቃል የገባው ሀገሬ ቴሌቪዥን አሁን ደግሞ የጀርመን ቡንደስሊጋ ስርጭትን ይዞ ብቅ ብሏል።
በኢትዮጵያ የግል ሚዲያ ታሪክ ግዙፍ የስፖርት ኹነቶችን እያደረሰ ያለው ጣቢያው፣ የ2026/27 የጀርመን ቡንደስሊጋ የነፃ አየር ስርጭት (FTA) ብቸኛ ባለመብት በመሆን አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል።
በዚህም መሠረት የሀገራችን የስፖርት አፍቃሪዎች ያለምንም ክፍያ በቤታቸው ሆነው የጀርመንን የኳስ ጨዋታዎች መከታተል የሚችሉበት ዕድል ተመቻችቶላቸዋል።
ሀገሬ ቴሌቪዥን በዚህ የውድድር ዓመት
በየሳምንቱ ቅዳሜ ከምሽቱ 1፡30 ላይ የሚደረጉ የተመረጡ የቡንደስሊጋ ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ወደየ ቤቱ የሚያደርስ ይሆናል።
ከጨዋታዎቹ በተጨማሪም ዘወትር አርብ ምሽት ሳምንታዊ የጨዋታዎች ትንተና እና ዝግጅት የሚያቀርበውን የቅድመ-ጨዋታ ፕሮግራም፣ ሰኞ ምሽት ደግሞ የሳምንቱን ሙሉ ጨዋታዎች ግቦችና ምርጥ እንቅስቃሴዎች ያካተተውን ማጠቃለያ ያስተላልፋል።
እንዲሁም ረቡዕ ምሽት በፕሪሚየር ሊጉ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ሳቢና ማረኪ የዘጋቢ ፊልሞች ታሪኮችን በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ተመልካቾች በነፃ የሚያቀርብ በመሆኑ የስፖርቱ አፍቃሪዎች በቤታቸው ሆነው የተሟላ የኳስ ድግስ እንዲኮመኩሙ ተጋብዘዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.