የ18 ዓመቱ ወጣት ኤልያስ ገበየሁ ታዬ መጥፋቱ ተገለፀ፤

- Advertisement -
Sidebar AD

* ፖሊስ ህብረተሰቡ የትብብር ድጋፍ እንዲያደርግ ጠየቀ

#Ethiopia | ​በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ክልል ልዩ ቦታው ብስራተ ኤልያስ አካባቢ የሚኖረው የ18 ዓመቱ ወጣት ኤልያስ ገበየሁ ታዬ ከቤት እንደወጣ ሳይመለስ መቅረቱን የአካባቢው ፖሊስ መሪያ ቤት አስታውቋል።

​አባቱ አቶ ገበያሁ ታዬ በገጃ ሰፈር አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው ባስመዘገቡት አቤቱታ መሰረት፣ ወጣቱ በ19/12/2018 ዓ.ም ከቤት የወጣ ሲሆን እስካሁን ድረስ ያለበት ቦታ አልታወቀም። ጉዳዩ በሁነት ማጣሪያ መዝገብ ቁጥር 02/18/19 ተመዝግቦ የፍለጋ እና የክትትል ስራ እየተከናወነ ይገኛል።

​የልደታ ዋና ፖሊስ መምሪያ የወንጀል እና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ክፍል የጠፋውን ወጣት ፎቶግራፍ በመበተን በቴሌቪዥንና በሌሎች መገናኛ ብዙኃን እንዲተላለፍ እና ህብረተሰቡ መረጃ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪ አቅርቧል።

​ወጣቱን ያየ፣ ያለበትን የሚያውቅ ወይም ማንኛውንም ጠቃሚ መረጃ ያለው ሰው በሚከተሉት የፖሊስ ስልክ ቁጥሮች በመደወል ትብብር እንዲያደርግ ጠየቋል፦

​የገጃ ፖሊስ ጣቢያ መረጃ ስልክ፡ 0112300436

​የልደታ ዋና ፖሊስ መምሪያ፡ 0116556150

የፈላጊ ቤተሰቦቹ ስልክ ቁጥር
0935871945
0962211918
0911780839

#ሼር # Share

​#MissingPerson #Ethiopia #AddisAbaba #LidetaSubcity #HelpFindSeysay





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: