ጆኒ ተጋጣሚውን ሴዶን በመጀመሪያው ዙር በመርታት የMMA የክብር ቀበቶውን ተቀዳጀ

- Advertisement -
Sidebar AD

#​Ethiopia | በዓድዋ ድል መታሰቢያ በተካሄደው ደማቅ የድብልቅ ማርሻል አርት (MMA) ውድድር ጆኒ ተጋጣሚውን ሴዶን በመጀመሪያው ዙር በፍጥነት በማሸነፍ የክብር ቀበቶውን ተረክቧል።

​በተደራጀ የመድረክ ዝግጅት፣ በታዳሚዎች ደማቅ ተሳትፎና በስፖርተኞች ብርቱ ፉክክር የተካሄደው “አድዋ ፋይት ናይት 2” የሀገራችንን የማርሻል አርት ውድድር ደረጃ ከፍ ባደረገ መልኩ ተጠናቋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ከዋናው የMMA ፍልሚያ በተጨማሪ የቦክስ እና የሞይታይ (Muay Thai) ውድድሮች ተካሂደው የተመልካቹን ቀልብስበዋል።

​በዕለቱ ታዋቂ አርቲስቶች፣ የቲክቶክ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችና በርካታ የስፖርት አፍቃሪዎች በተገኙበት ጆኒ የበላይነቱን በማስመስከር የደማቁ ምሽት አሸናፊ መሆን ችሏል።

​#MMA #AdwaFightNight #AdwaFightNight2 #Johnny #EthiopiaMMA #MartialArts





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: