6 አመታትን ቁርሱን ሳይበላ ቆጥቦ ያሳተመው “እነሆ የምለው” የተሰኘ የግጥም ሊመረቅ።

- Advertisement -
Sidebar AD

በገጣሚ መለሰ ኪዳኔ የተደረሰው እነሆ የምለው የተሰኜ የግጥም መድብል ታትሞ ለንባብ ይፋ ሆኗል። እነሆ የምለው የግጥም መድብል ታሪክን፣ ባህልን፣ ፍቅርን እንዲሁም ማንነትን በማንጸባረቅ የትውልድን ድምጽ የሚያስተጋቡ ግጥሞች ስብስብ ነው።

እነሆ የምለው የግጥም መድብልን ለ 6 አመታት ቁርሱን ሳይበላ ቆጥቦ ለህትመት እንዳበቃው ሲናገር ገጣሚው በመንግስት ደሞዝ መጽሀፍ ማሣተም ከባድ ቢሆንም ከታሰበበት ግን የማይቻል የለም ብሏል።

ስለ መድብሉ ጸሀፊ ተውኔትና ባለቅኔ አያልነህ ሙላቱ ቆንጆ ምስክርነት የሰጡት ሲሆን እውናዊ ታሪኮች በመወድስ የአጻጻፍ ስልት ተሰንደውበታል። ከግጥሞቹ መሀል ፍቅር በገጠር፣ አድዋ፣ ሴተኛ አዳሪ ናት፣ የምስራቋ ፀሐይ፣ ሸዋን ተዋወቁት፣ ብራምባሯን ባገኝ እንዲሁም በወጣቶች የሱስ ህይወት ላይ የሚያጠነጥን ቁራኛ የተሰኘ ግጥሞች ተጠቃሽ ናቸው።

እነሆነ የምለው የግጥም መድብል ቅዳሜ ነሀሴ 23 አ አ ለም ሆቴል አካባቢ በሚገኘው ቫምዳስ ሲኒማ አንጋፋና ወጣት የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በተገኙበት በድምቀት ይመረቃል። ውድ የጥበብ አፍቃሪያን በሙሉ ተጋብዛችኋል።




Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2