#FastMereja | የሀገር ውስጥ አቅምን በማጎልበት ረገድ የሚጠቀሰው ሳሬም ፈርኒቸር ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶቹን ለደንበኞች ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ያለመውን 3ኛ ቅርንጫፉን ዛሬ ነሐሴ 23 ቀን 2018 ዓ.ም በቦሌ ቡልቡላ በይፋ ከፈተ። በዚሁ የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የንግድ አጋሮች፣ የስራ አመራሮች፣ የዲጂታል ሚዲያ ባለሙያዎችና የይዘት ፈጣሪዎች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል።
ተቋሙ የመክፈቻ ስነ-ስርዓቱን አስመልካች በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ የአዲሱ ቅርንጫፍ መከፈት ተራ የንግድ ማስፋፊያ ሳይሆን የሀገር ውስጥ የማምረት አቅምን በማሳደግ ከውጭ የሚገቡ የፈርኒቸር ምርቶችን በሀገር በቀል ምርት ለመተካት የተያዘውን ሀገራዊ ግብ ለማሳካት ትልቅ ማሳያ ነው። ሳሬም ፈርኒቸር ጥንካሬን፣ ዘላቂነትን፣ ምቾትን እና ፍትሃዊ ዋጋን መለያው በማድረግ የደንበኞቹን ፍላጎት በጥራት ለማሟላት እየሰራ ይገኛል ተብሏል።
ድርጅቱ ቀደም ሲል በቃሊቲ የመጀመሪያውን እንዲሁም በለቡ ሁለተኛውን ቅርንጫፍ ከፍቶ ለአገልግሎት ያበቃ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለት በቡልቡላ ያስመረቀው ሶስተኛ ቅርንጫፉ የዚሁ የማስፋፊያ እቅድ አካል ነው። አሰራሩን አጠናክሮ በመቀጠል በቀጣይ አራተኛ እና አምስተኛ ቅርንጫፎቹን ለመክፈት ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ከውጪ የሚመጡ የተጠናቀቁ የፈርኒቸር ውጤቶችን በሀገር ውስጥ ምርቶች የመተካት ዋነኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ያለው ድርጅቱ፣ በዚህ እንቅስቃሴው ለበርካታ ዜጎች አዲስ የስራ ዕድል መፍጠር ችሏል። ድርጅቱ በንግድ ጉዞው ለደረሰበት ስኬት ትልቁ ሀብቱ ደንበኞቹ መሆናቸውን ጠቅሶ፣ በቀጣይም ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶችን በታማኝነት ማቅረቡን እንደሚቀጥል ተነግሯል። #ቢዝነስ



Source: FastMereja








No comments yet.