በኔፓል የጎርፍ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ600 በላይ ደረሰ

- Advertisement -
Sidebar AD

በኔፓል እና ቲቤት ድንበር ላይ በደረሰው የጎርፍ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 626 መድረሱን የአገሪቱ ብሔራዊ የአደጋ ቅነሳ እና አስተዳደር ባለሥልጣን አስታወቀ።
ባለሥልጣኑ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ ባጋራው መረጃ መሠረት 2ሺህ 426 ሰዎች አሁንም ድረስ የደረሱበት እንደማይታወቅ ይፋ አድርጓል።
ፖሊስ ቀደም ብሎ 616 ሰዎች መሞታቸውን ገልጾ የነበረ ቢሆንም የባለሥልጣኑ መረጃ የሟቾች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ መምጣቱን ያሳያል።
የደረሱበት ያልታወቁ ሰዎች ቁጥርም ከነበረበት 1,924 በፍጥነት ጨምሯል።

በጎርፍ አደጋው 517 የውጭ አገር ዜጎች የጠፉ ሲሆን ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶች ከመንግሥት የሚወጡ መረጃዎችን በቅርበት እየተከታተሉ ነው።
ኔፓል ከቻይና ጋር በምትዋሰንበት ድንበር አቅራቢያ በደረሰው የጎርፍ አደጋ የሞቱ እና የጠፉ ሰዎችን እየፈለገች ባለችበት አራተኛ ቀን ያጋጠመው የአየር ጠባይ በሂሊኮፕተር የሚደረግ ሃሰሳን አስተጓጉሏል።
የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች እና ወታደራዊ ባለሥልጣናት ከረቡዕ ጀምሮ በአደጋው የተጎዱ እና የሞቱ ሰዎችን ለማውጣት እየሰሩ ነው።

የተወሰኑ ከአደጋው የተረፉ ሰዎች ከጭቃ ውስጥ ማውጣት የተቻለ ሲሆን የሕይወት አድን ሠራተኞች የጠፉ ሰዎችን ለማግኘት የተለያዩ ሥፍራዎች ላይ ሃሰሳ እያደረጉ ነው።
የኔፓል ጦር ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጄነራል ራጃ ራም ባስኔት ቅዳሜ ማለዳ የአየር ሁኔታው እስኪሻሻል ድረስ በሂሊኮፕተር የሚደረግ ፍለጋ ለጊዜው መቆሙን ተናግረዋል::

BBC





Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2