#Ethiopia | አሜሪካ 200 የሚጠጉ ወታደሮቿን ከናይጄሪያ ልታስወጣ ነው።
አሜሪካ በመስከረም ወር ላይ 200 የሚጠጉ ወታደሮቿን ከናይጄሪያ ለማስወጣት ዝግጅት እያደረገች መሆኑን የአሜሪካ ወታደራዊ ባለስልጣናትን ጠቅሶ አልጀዚራ ፅፏል።
ከአሜሪካ ዘደ ናይጄርያ የተላከው ይህ የጦር ሰራዊት በዋናነት በመረጃ በክትትል እና በፀረ ሽብርተኝነት ድጋፍ ላይ ትኩረት አድርጎ ሲሰራ የቆየ ነው።
በትንሽ ቁጥር የተደራጁ የአሜሪካ አሰልጣኞች እና የደህንነት አባላት አሁንም እዚያው እንደሚቆዩ ተገልጿል።
የአሜሪካ የአፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄነራል ዳግቪን አንደርሰን እንደተናገሩት በቻድ ተፋሰስ በተካሄደ ወታደራዊ ዘመቻ ከፍተኛ የሽብርተኛ ድርጅቶች መሪ የሆነው አቡ ቢላል አል-ሚኑኪ ከተገደለ በኋላ በርካታ የአሜሪካ ወታደሮች አስቀድመው መውጣት መጀመራቸውን አረጋግጠዋል።
ጄነራል አንደርሰን አክለውም ዘመቻው የቡድኑን አመራር በእጅጉ ያዳከመ መሆኑን ገልጸው፣ ከናይጄሪያ ጋር የሚደረገው የመረጃ ልውውጥ ትብብር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ወታደሮቹ ቢወጡም ዋሺንግተን ከናይጄሪያ ጋር ያላትን የደህንነት ትብብር አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልጻለች።
በአነስተኛ ቁጥር የተደራጁ የአሜሪካ አሰልጣኞች፣ የደህንነት አባላት እና የመረጃ ልውውጥ ትብብሮች እዚያው እንደሚቀጥሉ ተነግሯል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#America #AFRICOM
#Nigeria #troops
#peace #security
#Cooperation #military
Source: GetuTemesgen








No comments yet.