ከምድር በታች በሚገኝ ጥልቅ ሥፍራ ለሚሊዮን ዓመታት የኖረው ‘የዲያቢሎስ ትል’

- Advertisement -
Sidebar AD

መሬትን በጥልቅ ቆፍረን የምድር ውስጠኛ ክፍል (ክረስት) የሚባለው ላይ ብንደርስ የምንመለከተው ነገር ምቾት የሚሰጥ አይሆንም።

የፀሐይ ብርሃን እየጠፋ ሲሄድ እና የቀለጠ አለት ወደ ሚገኝበት የምድር እምብርት ስንጠጋ የሙቀት መጠኑ እና ግፊቱ እየጨመረ ይሄዳል።

ነገር ግን ከመሬት በታች በ1.3 ኪ.ሜ ጥልቀት ውስጥ ሕይወት ያለው ነገር አይገኝም ብለው ካሰቡ ተሳስተዋል።

በቢሊየኖች የሚቆጠሩ ትሎች አንዳንድ ጊዜ ደማቅ ብርቱካናማ ወይም ነጭ ምንጣፎችን ፈጥረው ይገኛሉ።

በአጉሊ መነጽር ሲታዩም ትንሽ ትል በአፉ ላይ ሹል ነገሮችን በመጠቀም ሲንቀሳቀስ ይታያል።
ይህ ሃሊሴፋሎበስ ሜፊስቶ (Halicephalobus mephisto) ወይም ‘ዲያብሎስ ትል’ በመባል የሚታወቀው ሲሆን ረቂቅ ተሕዋስያንን ለማግኘት ይሯሯጣል።

ምንም እንኳን ቅንጣት የሚያክል ቢሆንም በሚኖርበት ሥነ ምኅዳር ውስጥ ዓሣ ነባሪ ማለት ነው።

በሚሞትበት ወቅትም አካሉ ለትሎች እና ለሌሎች ሕይወት ላላቸው ነገሮች ምግብነት ይውላል።
ይህም የዚህን ትል የሕይወት ዑደት ለማስቀጠል ይረዳል።

እንደ አውሮፓውያኑ ከ1980ዎቹ በፊት፣ አብዛኛዎቹ የሥነ ሕይወት ባለሙያዎች ሕይወት ከመሬት 30 ሴንቲ ሜትር በታች ይኖራል ብለው አያስቡም ነበር።

ዘገባው የቢቢሲ ነው


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2