የኤርትራውያን አንድነት ለሀገር ክብር፡ በሚስ ወርልድ 2026 ታሪክ የሰራው የህዝብ ድምጽ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I በሚስ ወርልድ 2026 (Miss World 2026) ውድድር ላይ ኤርትራን ለመጀመሪያ ጊዜ በመወከል ላይ የምትገኘው ተወዳዳሪ ስኒት ሀብተአብ፣ በህዝብ ድምጽ አሰጣጥ ክፍለ አህጉራዊ መሪነቱን በከፍተኛ ልዩነት መያዟን ተከተሎ፣ በዓለም ዙሪያ የሚኖሩ ኤርትራውያን ዲያስፖራዎች ያሳዩት አገራዊ ደጋፊነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ትኩረት ስቧል። በፖለቲካዊ አመለካከትም ሆነ በስደት ምክንያት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚኖሩ ኤርትራውያን፣ በሀገራቸው ብሄራዊ ክብር እና መድረክ ላይ ምንም ዓይነት ልዩነት እንደሌላቸው በግልጽ አሳይተዋል።

​በቪየትናም አስተናጋጅነት እየተካሄደ ባለው የ75ኛው ሚስ ወርልድ ውድድር ላይ ስኒት ሀብተአብ ከአፍሪካ ክፍለ አህጉር በህዝብ ድምጽ የመሪነቱን ቦታ የያዘች ሲሆን፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከ5 ሚሊዮን በላይ ነጥቦችን በማሰባሰብ የሁሉንም ቀልብ ስባለች። በነቭሮሳይንስ እና በልዩ ፍላጎት ትምህርት የተሰማራችው ይህች ተወዳዳሪ፣ የሀገሯን ስም ለመጀመሪያ ጊዜ በታሪክ ወደ ሚስ ወርልድ መድረክ በማውጣት ረገድ ትልቅ ሚና ተጫውታለች።

​የፖለቲካ ልዩነታቸውን ወደ ጎን በመተው በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኤርትራውያን በዲጂታል ድምጽ መስጫ ኮምፒውተሮች እና ስልኮች አማካኝነት ያደረጉት የተቀናጀ የድምጽ ማሰባሰብ ዘመቻ ለውጤቱ መገኘት ዋነኛ ምክንያት ሆኗል። የውድድሩ የመጨረሻ ምዕራፍ እና የህዝብ ድምጽ አሰጣጥ ለሚቀጥሉት አምስት ቀናት የሚቀጥል ሲሆን፣ የስኒት ሀብተአብ ስኬት የኤርትራውያንን ጠንካራ አገራዊ አንድነት እና ለሀገራዊ መድረኮች ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያስመሰክር እንደሆነ ተገልጻል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: