#Ethiopia | በሙዚቃ ስራዎቹና የሚታወቀው ተወዳጁ ድምፃዊ አስገኘው አሽኮ (አስጌ) በአዲሱ ዓመት “እንቁዎች” በተሰኘ አዲስ የመዝናኛ ፕሮግራም ወደ ቴሌቪዥን መስኮት ሊመጣ ነው።
አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ “ጤንነትዎን እንሸልምዎ” በሚል መሪ ቃል ከሚያቀርባቸው አዳዲስ ፕሮግራሞች መካከል አንዱ በሆነው በዚህ ዝግጅት ላይ፣ ድምፃዊው የተለመደውን አዝናኝ፣ ቀልደኛና ሳቅ አፍላቂ ክህሎቱን አጣምሮ ለተመልካቾች እንደሚያካፍል ይጠበቃል።
ባህላዊ የሙዚቃ ቅኝቶችን ከዘመናዊ አቀራረብ ጋር በማዋሃድ በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ የራሱን አሻራ ያሳረፈው አስጌ፣ በተለይም “ደንዳሾ” በተሰኘው ስራው ከፍተኛ ተወዳጅነትን ማትረፉ ይታወሳል።
ከዚህም በተጨማሪ “ያድሴ”፣ “ባሌ ሮቤ”፣ “ኑደሬ ጋሞ ጎፋ”፣ “ዱማ ዱሜ” እና “ሎሽኬ” የመሳሰሉ ተወዳጅ ዜማዎችን ለአድማጮች ያበረከተ ሲሆን፤ ከቤቲ ጂ፣ ማይኮ፣ እፀገነት ኃይለማርያም፣ እንዲሁም እንደ ማህሙድ አህመድ ከመሳሰሉ አንጋፋና ታዋቂ አርቲስቶች ጋር በጋራ ሰርቷል።
የድምፃዊው ተሳትፎ በአገር ውስጥ ብቻ ሳይገደብ፣ በ’ኮክ ስቱዲዮ አፍሪካ’ መድረክ ከኡጋንዳዊቷ ድምፃዊት ሺባሕ ጋር በመጣመር የኢትዮጵያን የሙዚቃ ባህል ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በማስተዋወቅ ስኬታማ ስራ ሰርቷል።
በአገር ውስጥም ሆነ በአህጉር አቀፍ ደረጃ በሙዚቃው ዘርፍ ደማቅ ጉዞን ያደረገው አርቲስቱ፣ አሁን ደግሞ ከሙዚቃ መድረክ ባለፈ በቴሌቪዥን ፕሮግራም አዲስ የመዝናኛ ቀለም ይዞ ብቅ በማለት የተመልካቾችን የአዲስ ዓመት ቆይታ በሳቅና በፈገግታ ለማድመቅ ዝግጅቱን አጠናቋል።
(via amn)
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.