32 ኤርትራውያንና 3 የሰዎች አዘዋዋሪዎች በአርባምንጭ ተያዙ።በሕገወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ 32 የኤርትራ ዜጎች ሁለት ተቀ…

- Advertisement -
Sidebar AD
32 ኤርትራውያንና 3 የሰዎች አዘዋዋሪዎች በአርባምንጭ ተያዙ።
በሕገወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ 32 የኤርትራ ዜጎች ሁለት ተቀባይና አንድ አሽከርካሪ ከነ ተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የአርባምንጭ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ክበበው አዳል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቀዋል።
‎ኤርትራዊያኑ መነሻቸውን ከመሃል ሀገር በማድረግ በአርባምንጭ ኮንሶ ጂንካ በኩል ወደ ኬንያ ለመሸጋገር ሲንቀሳቀሱ እንደነበር የገለጹት ኮማንደር ክበበው፣ ከሕብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማና በፀጥታ መዋቅሩ ቅንጅታዊ ክትትል በሲቀላ ክ/ከተማ ነጭ ሳር ቀበሌ ሲያትል አልጋ ቤት ግራውንድ ስር ባለ አዳራሽ ፍራሾችን በመጣል ከተሸሸጉበት መያዛቸውን ተናግረዋል።

በአጠቃላይ ‎11 ወንዶች፣ 14 ሴቶች እና 7 ህጻናት በድምሩ 32 ኤርትራውያን ናቸው የተያዙት።
በተጨማሪ ሁለት አዘዋዋሪዎች እንዲሁም ስደተኞችን ወደ አርባ ምንጭ ያመጣ የሰሌዳ ቁጥር ” ኮድ 3-23042 አአ ” ሀይሩፍ መኪናና አሽከርካሪውን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አዛዡ አስታውቀዋል።

‎በተዘዋዋሪዎቹ ዙሪያ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑንና ስደተኞቹን ለክልሉ ፖሊስ አሳልፎ የመስጠት ሂደት እንደሚከናወን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1