#FastMereja I በጎፋ ዞን ሳውላ አጠቃላይ ሆስፒታል አንዲት እናት በአንድ ጊዜ አራት ህፃናትን በሰላም መገላገሏ ተነገረ።
በሳውላ አጠቃላይ ሆስፒታል ተገቢው ምርመራ ከተደረገላት በኋላ ለተከታታይ አምስት ቀናት በቅርብ የሕክምና ክትትል ስር ቆይታ ወሊዱን ያከናወነችው እናት፣ በአሁኑ ወቅት ከነሙሉ ጤንነታቸው ከ አራቱም ህፃናት ጋር በጥሩ ሁኔታ ላይ ትገኛለች።
የማህጸንና ጽንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ግላንደ ጊሎ እንደገለጹት፣ በሆስፒታሉ ደረጃ ሁለት እና ሦስት ህፃናትን በአንድ ጊዜ ማዋለድ የተለመደ ቢሆንም፣ በአንድ ወሊድ አራት ህፃናትን በሰላም ማዋለድ መቻሉ በሆስፒታሉ ታሪክ የመጀመሪያው ነው።
የህፃናቱ አባት አቶ ናፍቆት ቡሼ በበኩላቸው፣ ከዚህ ቀደም የአምስት ሴት ልጆች አባት እንደነበሩ አጋልጠው፤ ባለቤታቸው አሁን ደግሞ ተጨማሪ አራት ሴት ህፃናትን በሰላም በመገላገሏ በአጠቃላይ የዘጠኝ ሴት ልጆች አባት መሆን መቻላቸውን ገልጸዋል። አባት አቶ ናፍቆት አክለውም በአንድ ጊዜ አራት ህፃናትን ማግኘት ያልተለመደና እጅግ አስደሳች እንግዳ ክስተት እንደሆነባቸው ተናግረዋል ሲል ጎፋ ቴሌቪዥን ነው የዘገበው።
Source: FastMereja








No comments yet.