#Ethiopia | ተመራቂዎቹ በድኅረ-ምረቃ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን እና በፕሮጄክት ማኔጅመንት እንዲሁም በተለያዩ የቅድመ-ምረቃ መስኮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።
ኩዊንስ ኮሌጅ በ26ኛው የምርቃት ዙሩ በድህረ-ምረቃ በመጀመሪያ ዲግሪ እና በቴክኒክና ሙያ (TVET) ያሰለጠናቸውን 4,219 ተማሪዎች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ አስመርቋል።
በ1990 ዓ.ም. በአራት ሠራተኞች ሥራ የጀመረው ኮሌጁ ባለፉት 29 ዓመታት ከ54 ሺህ በላይ ተማሪዎችን አስተምሮ ያበቃ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከ500 በላይ ሠራተኞች አሉት።
ተመራቂዎቹ ከአየርጤና፣ ዮሐንስ (ፒያሳ)፣ ሜክሲኮ፣ ቃሊቲ፣ ሃናማሪያም፣ ኮልፌ፣ አስኮ ካምፓሶች እና በርቀት ትምህርት (763 ተማሪዎች) የሰለጠኑ ናቸው።
የኮሌጁ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ዶ/ር ሞገስ ግርማ ተመራቂዎች ራስን መግራት፣ ቅንነትና እግዚአብሔርን መፍራት እንዲሰንቁ ሲመክሩ፤ የሜሪ ጆይ መስራች ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ ደግሞ ምርቃት የቀጣይ እውቀትና ኃላፊነት መጀመሪያ መሆኑን አሳስበዋል።
ኮሌጅ ዘንድሮ ለ26ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ነው ያስመረቀው።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen



Source: GetuTemesgen









No comments yet.