የደባርቅ ከተማ የኮሪደር ልማት ከ450 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብና የአይነት ድጋፍ ተገኘበት

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የደባርቅ ከተማን የቱሪዝም መስህብነት ለማሳደግና ጽዱ ለማድረግ የተጀመረው የኮሪደር ልማት የበርካታ ወገኖችን ትብብር በማግኘት ላይ ይገኛል።

ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓም በተካሄደው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር የክልሉ ፕሬዚዳንት አረጋ ከበደ እንዲሁም ሌሎች የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ባለሀብቶች ተገኝተዋል።

በዕለቱ በተካሄደው የሃብት ማሰባሰብ ሂደት በጥሬ ገንዘብና በአይነት ከ450 ሚሊዮን ብር በላይ ማሰባሰብ የተቻለ ሲሆን ድጋፉ አሁንም ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል።

በዚህ ታላቅ መድረክ የሬማ ኮንስትራክሽን ባለቤት አቶ ፍቅሬ 20 ሚሊየን ብር አቶ በላይነህ ክንዴ 10 ሚሊየን ብር እንዲሁም ቢአይካ 15 ሚሊየን ብር በመለገስ ከፍተኛ አጋርነታቸውን አሳይተዋል።

ይህ የልማት እንቅስቃሴ ደባርቅን በቱሪዝም በንግድና በኢንቨስትመንት ዘርፍ የበለጠ ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚያስችል ሲሆን ባለሀብቶችም በአካባቢው ባሉ አማራጮች ላይ እንዲሰማሩ ጥሪ ተ አስተላልፏል።

በቀጣይም የከተማዋን ነዋሪዎችና ደባርቅን የሚወዱ አካላትን ያካተተ ሰፊ የልማት ምዕራፍ እንደሚቀጥል የከተማዋ ልማት ኮሚቴ አስታውቋል።

#ደባርቅ #ኮሪደርልማት #ቱሪዝም #ኢንቨስትመንት #አማራክልል #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: