በሰማይ የተከሰተው የብርሃን ምስጢርና የነዋሪዎች ስጋት!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በቅርቡ በጃፓን የባህር ዳርቻ ሰማይ ላይ ከየት መጡ ያልተባሉ እንደ ግዙፍ የብርሃን አምድ የተተከሉ ምስጢራዊ ጭረቶች በድንገት ብቅ አሉ።

ምሽቱን ዘና ብለው ሰማዩን የተመለከቱ ነዋሪዎች ዓይናቸውን ማመን አቅቷቸዋል።

ከተማዋ በአንዴ በድንጋጤ ታመሰች።

ማህበራዊ ሚዲያውም “ከሌላ ፕላኔት የመጡ እንግዶች ምድርን ሊወሩን መጡ የዓለም መጨረሻ ደረሰ እንዴ? በሚሉ አስደናቂና አዝናኝ ግምቶች በሰከንዶች ውስጥ ተጥለቀለቁ።

አንዳንዶቹማ እንኳን ደስ አላችሁ የሳይንስ ፊልሙ ወደ እውነተኛ ሕይወት ተቀየረ በማለት በቪዲዮዎቻቸው ላይ ቀልድ ቀላቅለው ማሰራጨት ጀምረው ነበር።

ነገር ግን ነገሩ ሌላ ሆነ።

ሳይንቲስቶች የነዋሪዎችን ስጋትና የኢንተርኔቱን አማካኝነት የተፈጠረው ውካባ ከተመለከቱ በኋላ ፈገግ ብለው ምስጢሩን ይፋ አደረጉ።

በከባቢ አየር ውስጥ በጣም ቀዝቃዛ የበረዶ ክሪስታሎች በመኖራቸው በባህር ላይ ዓሳ በማጥመድ ላይ የነበሩ ጀልባዎች የለቀቁት ብርሃን በእነዚህ የበረዶ ክሪስታሎች ላይ ማንጸባረቁ ተከትሎ ነው ይህ የተፈጠረው ብለዋል።

ነገሩ የጠፈር ፍጥረታት ወረራ ሳይሆን ተፈጥሮና የሰው ልጅ የሠሩት አስገራሚ የብርሃን ጂምናስቲክ ነበር አሉ።

በሁኔታው የተደናገጡት ነዋሪዎችም ምስጢሩ ሲሰሙ ድባቡን እንደገና ወደ ሳቅና ቀልድ ቀየሩት።

ተፈጥሮ አንዳንዴ ከፊልሞች በላይ ድንቅ ድራማ መስራት እንደምትችል ያሳየ አስገራሚ ምሽት ሆኖ አልፏል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen
#Japan #scientists #fish


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2