በአዲስ አበባ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት 500 ሺህ መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት መታቀዱ ተገለጸ #የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር …

- Advertisement -
Sidebar AD
በአዲስ አበባ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት 500 ሺህ መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት መታቀዱ ተገለጸ

#የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት በየዓመቱ 100 ሺህበአጠቃላይና 500 ሺህ መኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ ለቤት ፈላጊዎች ለማቅረብ ማቀዱን አስታወቀ።
የቢሮው ኃላፊ ወይዘሮ ቅድስት ወልደጊዮርጊስ ለአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እንደገለጹት ከተማ አስተዳደሩ የነዋሪዎችን ከፍተኛ የመኖሪያ ቤት ፍላጎት በዘላቂነት ለመፍታት እና አቅርቦትን ከፍላጎት ጋር ለማጣጣም ሰፊ ጥረት እያደረገ ይገኛል። በመጪዎቹ አምስት ዓመታት የሚከናወነው የቤት ልማት ስራም ይህንን ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት የተነደፈ ዋና ስትራቴጂ መሆኑን ጠቁመዋል።
ቢሮው ባለፉት አምስት ዓመታት ባከናወናቸው ሁለገብ የቤት ልማት ስራዎች ከ496 ሺህ በላይ መኖሪያ ቤቶችን መገንባት መቻሉን ኃላፊዋ አስታውቀዋል። ይህ ስኬት የተመዘገበው የመንግስትን ጥረት ብቻ ሳይገድብ፣ የግሉን ዘርፍ በስፋት ማሳተፍ በመቻሉ እንደሆነ ተብራርቷል።
በተለይም ሪል ስቴቶች ወደ ልማቱ እንዲገቡ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር፣ ማህበራትን ማደራጀት፣ የ40/60 እና የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤት ተጠቃሚዎችን እንዲሁም የመንግስት ሰራተኞችንና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ባካተተ መልኩ ወደ ቤት ልማቱ እንዲገቡ መደረጉ ተገልጿል።
#ከመንግስት በጀት ግንባታዎች ጎንለጎን በመንግስትና በግል አጋርነት የተከናወኑ አዳዲስ የልማት ሞዳሊቲዎች ውጤት ማፍራታቸውንም የቢሮ ኃላፊዋ አክለው ገልጸዋል።በመጪው የአምስት ዓመት እቅድም የግሉን ዘርፍ ይበልጥ በስፋት በማሳተፍ የነዋሪዎችን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ምላሽ መስጠት ዋነኛው የትኩረት አቅጣጫ ሆኖ እንደሚቀጥል ተመላክቷል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1