በሱዳን ሰብዓዊ ጥሰት ፈፅመዋል የተባሉ የአር ኤስ ኤፍ መሪዎች ከእስራኤል ባለሥልጣናት ተገናኙበሱዳን የርስበርስ ጦርነት ውስጥ …

- Advertisement -
Sidebar AD
በሱዳን ሰብዓዊ ጥሰት ፈፅመዋል የተባሉ የአር ኤስ ኤፍ መሪዎች ከእስራኤል ባለሥልጣናት ተገናኙ‼️
በሱዳን የርስበርስ ጦርነት ውስጥ በመሳተፍ ላይ የሚገኙት የፈጣን ድጋፍ ኃይሎች (RSF) ከፍተኛ ባለሥልጣናት በግጭቱ ወቅት ወደ እስራኤል ምስጢራዊ ጉብኝቶችን ማድረጋቸውን «አፍሪካ ኢንቴሊጀንስ» ያወጣው የምርመራ ዘገባ አመላከተ።
መገናኛ ብዙኃኑ እንደገለጸው ከሆነ ከፈጣን ድጋፍ ኃይሎች ጋር ትስስር ያላቸው ሁለት ልዑካን ቡድኖች በመጀመሪያ በግንቦት 2017 ዓ.ም ለሁለተኛ ጊዜ ደግሞ በየካቲት 2018 ዓ.ም ወደ ቴል አቪቭ ተጉዘዋል።
ልዑካኑ ከእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች መመሪያ ባለሥልጣናት እና ከስለላ አገልግሎት ተወካዮች ጋር መክረዋል ተብሏል።
የመጀመሪያው ልዑክ የፈጣን ድጋፍ ኃይሎች ሁለተኛ ሰው እና የድርጅቱ መሪ የሙሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ ወንድም የሆኑትን አብዱል ረሒም ሐምዳን ዳጋሎን እንዲሁም ሌላኛውን የቤተሰብ አባል አልጎኔ ሐምዳን ዳጋሎን ያካተተ እንደነበር ተገልጿል።
ሁለቱ ግለሰቦች በየካቲት 2018 ዓ.ም በነበረው ሁለተኛ ጉብኝታቸው ወቅት ከድርጅቱ የሕግ አማካሪ ጋር በመሆን ወደ እስራኤል ተመልሰው እንደነበር ተጠቅሷል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1