ታሪካዊው ዲአፍሪክ ሆቴል በሐራጅ ሊሸጥ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል ሲጎተት የቆየውን የውርስ ክስ እልባት ለመስጠት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ችሎት ታሪካዊውን ዲ አፍሪክ ሆቴል በመጪው መስከረም ወር በሐራጅ ተሸጦ እንዲካፈል ውሳኔ መተላለፉን ከፎርቹን ጋዜጣ ሰምተናል።

ባለ ስድስት ፎቁ ሆቴል የቦታው መስራች በሆኑት በአቶ ሰይፉ ገብረዮሐንስ ወራሾች መካከል በአይነት ተከፋፍሎ ሊደርስ ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ንብረቱን በሐራጅ መሸጥን እንደ የመጨረሻ አማራጭ ለመውሰድ መገደዱ ተገልጿል።

በሜክሲኮ አደባባይ አቅራቢያ በ3,793 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ ያረፈው ይህ ሆቴል፣ ከአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምስረታ ጀምሮ የአህጉሪቱን መሪዎችና እንግዶችን ያስተናገደ ታሪካዊ ቅርስ መሆኑ ይታወቃል።

ፍርድ ቤቱ ለሐራጁ መነሻ የሚሆን ዋጋ ወደ 184 ሚሊዮን ብር ገደማ የተተመነ ቢሆንም የዘርፉ የዋጋ ግምት ባለሙያዎች ግን የሆቴሉ ታዋቂ ስምና ያለበት ስትራቴጂካዊ ቦታ ከግምት ሲገባ እሴቱ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ሊያወጣ እንደሚችል ይከራከራሉ።

ይህንን የተሰጠውን መነሻ ዋጋ በመቃወም የበኩር ልጅ ብስራት ሰይፉን ጨምሮ በርካታ ወራሾች ሐራጁ ከመካሄዱ በፊት ገለልተኛ የዋጋ ግምገማ እንዲደረግ ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ ለማቅረብ እየተዘጋጁ ይገኛሉ።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: