“አዲሱ የዓለም ስርዓት” መፅሐፍ ተመረቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I ​በኪንግ ታደለ ድሪባ የተደረሰዉና የአዕምሮ እንዲሁም የፍልስፍና ውጤት የሆነው “አዲሱ የዓለም ስርዓት” የተሰኘው አዲስ መፅሐፍ እሁድ ነሐሴ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በኩሪፍቱ ሪዞርት ተመርቋል።

​ይህ መፅሐፍ በዋናነት በዓለም ላይ የህዝቦች እኩልነት፣ ፍትህና ወንድማማችነት በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲሰፍን ከተፈለገ ዓለም በአንድ መንግስት፣ በአንድ ንጉስ እና በአንድ የገንዘብ ኖት ብቻ መመራት አለባት የሚለውን የፍልስፍና ሐሳብ መነሻ ያደረገ ነው ተብሏል። ጽሁፉ “ይህ አስተሳሰብ በምን መልኩ ወደ ተግባር ሊለወጥ ይችላል?” ለሚሉ ጥያቄዎች ሰፊ ምላሽ ለመስጠት ያለመ ሲሆን፣ ጉዳዩን ከኢኮኖሚ፣ ከመልከዓ ምድር፣ ከተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም፣ ከአካባቢ ጥበቃ፣ ከሐይማኖት፣ ከባህልና ከአጠቃላይ ማህበራዊ ጉዳዮች በስፋት ዳስሶ እንደሚያቀርብ ነው የተነገረው።

​መፅሐፉ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተደራሽ ለማድረግ ሲባል በአማርኛ፣ በእንግሊዝኛ እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች ተዘጋጅቶ ለንባብ የበቃ ሲሆን፣ በምረቃው ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙ ተጋባዥ እንግዶችና የዘርፉ ባለሙያዎች የመፅሐፉን ፍልስፍናዊ ይዘትና የቀረቡትን አማራጭ ሀሳቦች በተመለከተ ዳሰሳ እና ውይይት አድርገዋል።

#ኹነት






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1