የአድዋ ድልድይ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት ለትራፊክ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ተዘጋ

- Advertisement -
Sidebar AD

​በአዲስ አበባ ከተማ ለረጅም ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው የአድዋ ድልድይ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት ሊከሰት የሚችለውን አደጋ ለመከላከል ከሴቶች አደባባይ ወደ ባልድራስ ትራፊክ መብራት የሚወስደው መንገድ ከዛሬ ነሐሴ 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሁለቱም አቅጣጫ ሙሉ በሙሉ ለትራፊክ እንቅስቃሴ ዝግ መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን አስታወቀ።

​ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት በድልድዩ ላይ ያጋጠመው የመዋቅር ጉዳት በጥናትና ዲዛይን የተደገፈ ዘላቂ መፍትሔ እስኪያገኝ ድረስ መንገዱ ዝግ ሆኖ ይቆያል። የከተማዋ አሽከርካሪዎች በቦታው ላይ የሚከተለውን የትራፊክ መጨናነቅ ለማስቀረትና የእለት ተእለት እንቅስቃሴአቸውን ለማቃለል አማራጭ መንገዶችን በጥንቃቄ እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል። ባለሥልጣኑ የጥገናና የዘላቂ መፍትሔ ሥራው በተጠናቀቀ ጊዜ ተጨማሪ መረጃዎችን እንደሚያሳውቅ ገልጿል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1