📈 የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ገቢ በ2018 በጀት ዓመት 11.2 ቢሊዮን ዶላር ደረሰ
የመንግሥትን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ተከትሎ በ2018 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ ታሪካዊ ስኬት ማስመዝገቡን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።
🔹 ዋና ዋና ነጥቦች፦
የዕቅድ አፈጻጸም፦ በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ 9.4 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ 11.2 ቢሊዮን ዶላር በማግኘት የዕቅዱን 119 በመቶ ማሳካት ተችሏል።
በዘርፍ የተገኘ ገቢ፦ የማዕድን ዘርፍ 5.07 ቢሊዮን ዶላር በማስመዝገብ ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዝ፤ የግብርና ምርቶች 3.83 ቢሊዮን ዶላር፣ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ 493 ሚሊዮን ዶላር፣ እንዲሁም የኤሌክትሪክና ሌሎች ዘርፎች 425 ሚሊዮን ዶላር አስገኝተዋል።
ለስኬቱ ምክንያት የሆኑት፦ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው፣ የአፍሪካ ነፃ ንግድ ቀጣና ትግበራ፣ በሕገ-ወጥ ንግድ ላይ የተደረገ ቁጥጥር፣ የዋጋ ተመን ክለሳ እና የሎጀስቲክስ መሻሻሎች ለውጤቱ በዋናነት ተጠቀሰዋል።
@Seledadotio

No comments yet.