#Ethiopia | የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ በዛሬው እለት ግብጽ ገብተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ካይሮ የገቡት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ነው ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።
ፕሬዝዳንቱ ካይሮ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በግብጹ ፕሬዚዳንት አብደል ፈታህ አልሲሲ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ጉብኝቱ የሁለቱን ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እና አጠቃላይ ስትራቴጂካዊ አጋርነት የበለጠ ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
ሁለቱ መሪዎች በዋና ዋና ዘርፎች በተለይም በኢንፍራስትራክቸር በታዳሽ ኃይል በቴክኖሎጂ እና በሱዌዝ ካናል የኢኮኖሚ ቀጠና ውስጥ ይወያያሉ ተብሏል።
እንዲሁም በቻይና የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርጉና አዳዲስ የስምምነት ሰነዶችን እንደሚፈራረሙ ይጠበቃል።
ግብጽ በቻይና የመሰረተ ልማት እና የንግድ መስመር ዝርጋታ እቅድ ውስጥ በመካከለኛው ምስራቅና አፍሪካ ቁልፍ ስትራቴጂካዊ አጋር በመሆኗ አዳዲስ የጋራ ፕሮጀክቶችን መተግበር ላይ ይመክራሉም ተብሏል።
የፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዘመናትን የተሻገረ ወዳጅነት የሚያጠናክርና የሁለቱን ህዝቦች የጋራ ጥቅም ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ነው ሲሉ ባለሙያዎች ተናግረዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgn
#China #Egypt #Alsisi
#cooperation #Diplomacy #economy #Hornafrica
#Security #middleeast
Source: GetuTemesgen









No comments yet.