#Ethiopia | ጀርመን በሀይድሮጅን ነዳጅ የሚሰሩ ባቡሮችን ወደ ስራ አስገባች።
ሀገሪቷ “ኮራዲያ አይሊንት” የተሰኙት እነዚህ ባቡሮች ኤሌክትሪክ መስመሮችን ለመዘርጋት አስቸጋሪ በሆባቸው አካባቢዎች ነው አገልግሎት እንዲሰጡ አድርጋለች።
ባቡሮቹ አንድ ጊዜ ብቻ በተሞላ የሃይድሮጅን ነዳጅ እስከ 1,000 ኪሎ ሜትር ድረስ የመጓዝ አቅም አላቸው ተብሏል።
እነዚህ ባቡሮች የሃይድሮጅን ነዳጅ በመጠቀም ኤሌክትሪክ ያመነጫሉ።
ከባቡሩ የጭስ ማውጫ የሚወጣው የተለመደው ጭስ ሳይሆን የውሃ እንፋሎት እና የውሃ ጠብታዎች ብቻ ናቸው።
ባቡሮቹ በሚጓዙበት ወቅት ምንም ዓይነት ቀጥተኛ የካርቦን ዳይኦክሳይድ ጭስ አያወጣም ነው የተባለው።
በዚህም ጀርመን ሃይድሮጅን ባቡር ለመደበኛ የንግድ አገልግሎት ያዋለች በዓለም የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#German #hydrogen #gas
#powered #passenger #trains
#diesel #Condensation #CoradiaiLint
Source: GetuTemesgen








No comments yet.