#Ethiopia | የኡጋንዳዋ የጤና ሚኒስትር ሌቦችን ለመያዝ የሄዱበት ርቀት ውጤት አምጥቶለታል።
በኡጋንዳ የመንግሥት ሆስፒታሎች ውስጥ በሕመምተኞች ላይ የሚፈጸመውን ሕገ ወጥ የገንዘብ ብዝበዛና የእንግልት ጥቆማ የተከታተሉት የሃገሪቱ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ሳራ አቺየንግ ነገሩ ስር የሰደደ ነው ብለዋል።
ድርጊቱን እጅ ከፍንጅ ለመያዝ ራሳቸውን ተሸፋፍነው ተራ ታካሚ መስለው ባደረጉት አስደናቂ እንቅስቃሴ አዎንታዊ ውጤት ማስመዝገባቸው ተገለጸ።
ሚኒስትሯ በካምፓላ በሚገኘው ናጉሩ ሆስፒታል በድብቅ ባደረጉት ምልከታ የሕዝቡ የምሬት ምንጭ የሆኑ አንዳንድ የጤና ባለሙያዎች በመንግሥት ተቋማት ውስጥ ከፍተኛ ችግር እየፈጠሩ መሆናቸውን በገሃድ አረጋግጠዋል።
በነጻ ሊሰጡ የሚገባቸው የሕክምና አገልግሎቶች ላይ ክፍያ ሲጠየቅባቸው የቆዩት ዜጎች ምሬት ትክክለኛነት ያረጋገጡት ሚኒስትሯ ተራ ታካሚ ሆነው በቀረቡበት ወቅት በርካታ ችግሮች መኖራቸውን ነው የገለፁት።
ሚኒስትሯ በካፓላ ናጉሩ ሆስፒታል በነፃ የሚሰጡ ምርመራዎች ላይ ባለሙያዎች ከ150 ሺሊንግ በላይ አእያስከፈሉ እጅ ከፍንጅ ይዘዋል።
ሕገ ወጥ ክፍያውን ፈጽመው ከተቀበሉ በኋላ ወዲያውኑ ማንነታቸውን ይፋ ያደረጉት ሚኒስትሯ በሥፍራው ፖሊስ በመጥራት ጥፋተኞቹን በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ አድርገዋል።
ይህ የኡጋንዳዋ የጤና ሚኒስትር የሄዱበት ርቀትና የወሰዱት ቁርጠኛ እርምጃ በመልካም አስተዳደርና በተቋማት ተጠያቂነት ዙሪያ ለሌሎች አመራሮችም ትልቅ ማሳያና ትምህርት ሰጪ ልምድ መሆኑን ነው የተገለጸው።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#Uganda #health
#minister #Kampala
#Corrupt #workers
Source: GetuTemesgen









No comments yet.