#Ethiopia | ስዊድናዊው ባለሃብት ሮጀር አኬሊየስ በጋዛ ስትሪፕ የሚገኙ ህጻናትን የመማር እና ለደህንነት ቅነሳ የሚረዳ የ76 ሚሊዮን ዶላር (800 ሚሊዮን የስዊድን ክሮነር) ግዙፍ የበጎ አድራጎት እርዳታ ለተባበሩት መንግስታት (ዩኒሴፍ) አበረከቱ።
ይህ የቢሊየነሩ ልግስና የስዊድን መንግስት ቀደም ሲል መድቦት ከነበረው 400 ሚሊዮን ክሮነር ጋር የተጣጣመ ሲሆን፣ በጥቅሉ ለህጻናቱ የተሰበሰበውን የገንዘብ መጠን ወደ 1.2 ቢሊዮን የስዊድን ክሮነር (114 ሚሊዮን ዶላር) አድርሶታል።
ለአምስት ዓመታት የሚቆየው ይህ አጠቃላይ የድጋፍ ፕሮግራም በከባድ ችግር ውስጥ የሚገኙ የጋዛ ህጻናትን ህይወት በተለያዩ ዘርፎች ለመደገፍና የነገ ተስፋቸውን ለማለምለም ያለመ ነው።
በዚህም መሰረት ድጋፉ በዋናነት 400 ትምህርት ቤቶችን መልሶ በማጠናከር፣ የመምህራን ደመወዝ በመክፈል፣ ለተማሪዎች ምግብና የትምህርት ቁሳቁሶችን በማቅረብ ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።
ከዚህ በተጨማሪም ፕሮግራሙ ከትምህርት አቅርቦት ባሻገር ለህጻናቱ አስፈላጊውን የስነ-ልቦና እንክብካቤ፣ የንጹህ ውሃ አቅርቦት፣ የክትባት አገልግሎቶችን እንዲሁም አጠቃላይ የህጻናት ጥበቃ ስራዎችን በሰፊው የሚያካትት ነው።
ይህ የታላቅ ልግስና እርምጃ በችግር ውስጥ ላሉ የጋዛ ህፃናት ተስፋን ከማንገቡም በላይ አለም አቀፍ የጋራ ሰብአዊ ድጋፍን በማስተባበር ረገድ ትልቅ አርአያነት ያለው ተግባር ነው።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen








No comments yet.