#Ethiopia | ቢዮንሴ በኮሎምቢያ ለደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ 1 ሚሊዮን ዶላር ለገሰች።
ዝነኛዋ የሆሊውድ አርቲስት ቢዮንሴ በኮሎምቢያ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የሚሆን የ1 ሚሊዮን ዶላር ሰብአዊ እርዳታ ማድረጓን ይፋ አድርጋለች።
የቢዮንሴ የግል ኩባንያ የሆነው ፓርክዉድ ኢንተርቴይንመንት ባወጣው መግለጫ መሠረት ይህ የገንዘብ ድጋፍ በቀጥታ በአደጋው ለጎዱ ዜጎች ይውላል ብሏል።
ድጋፉ በዋነኝነት በአደጋው መጠለያቸውን ላጡ የምግብና የሕክምና እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች አስቸኳይ ድጋፍ ለማድረስ ይውላል ሲል ገልጿል።
በኮሎቢያ በቅርቡ በተከሰተው በዚሁ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከ300 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ የሚታወስ ነው።
እንዲሁም በሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ደግሞ መኖሪያቸውን ያጡ ሲሆን በርካታ መሰረተ ልማቶች መውደማቸው ይታወሳል።
ከቢዮንሴ በተጨማሪ እንደ ሻኪራ እና ካሮል ጂ ያሉ ታዋቂ የኮሎምቢያ ድምፃውያንም ለተጎጂዎች ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወቃል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen
#Colombia #earthquake
#Beyonce #PopSuperstar
#Humanitarian #Donation
Source: GetuTemesgen








No comments yet.