#Ethiopia | የክርስቲያኖ ሮናልዶ የመሪነት ባህሪ እና የሙያ ስኬት ከስፖርት ድንበር የተሻገረ ገጽታ አለው።
በንግድ፣ በፖሊሲ አወጣጥ፣ በቴክኖሎጂ እና በተለያዩ ድርጅታዊ መዋቅሮች ውስጥ ያሉ መሪዎች ከእሱ የስራ ፍልስፍና በርካታ ዋና ዋና ተግባራዊ ትምህርቶችን መውሰድ ይችላሉ።
ሮናልዶ ሁልጊዜ ከልምምድ ሰዓት ቀድሞ በመገኘት፣ በአመጋገብ እና በእረፍት ስነ-ምግባሩ ጥብቅ በመሆን እንዲሁም እስከ መጨረሻው ደቂቃ ድረስ በከፍተኛ ጥረት በመጫወት የቡድኑ አባላት ተመሳሳይ ቁርጠኝነት እንዲኖራቸው ያደርጋል።
የትኛውም መሪ ለድርጅቱ የሚያወጣው ከፍተኛ የስራ ጥራትና የዲሲፕሊን መስፈርት የሚጀምረው ከራሱ ባህሪ ነው።
መሪው ከቃላት በላይ በድርጊቱ ጠንካራ የስራ ባህል ሲያሳይ የድርጅቱ ሰራተኞች እና የስራ ባልደረቦች ያንን ከፍተኛ ስታንዳርድ ለመጠበቅ ይገደዳሉ።
በተጨማሪም ሮናልዶ የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድንን ከመቀላቀሉ በፊት ሀገሪቱ በታሪኳ አንድም አህጉራዊ ዋንጫ አልበላችም ነበር።
እሱ በመጣበት ዘመን ግን ማንኛውንም ታላቅ ቡድን ማሸነፍ እንችላለን የሚል አሸናፊ የአእምሮ ዝግጅት በማስቻል ታሪክ ቀይሯል።
በተመሳሳይ መልኩ ተስፋ የቆረጠ ወይም አነስተኛ ግብ ያለው የተቋም ባህልን ወደ አዲሱ ማድረግ እንችላለን የሚል አሸናፊ አእምሮ የመለወጥ ኃላፊነት የመሪዎች ድርሻ በመሆኑ አነስተኛ አቅም ያላቸውን ቡድኖች ትልቅ ግብ እንዲኖራቸው በማድረግ ተቋማዊ ሽግግር ማምጣት ይቻላል።
ሮናልዶ በሙያ ዘመኑ በርካታ ስሜታዊ ውረዶች፣ ጉዳቶች እና የደጋፊዎችና ሚዲያ ትችት ቢገጥመውም ትችቶችን በመቃወም ጊዜ ከማባከን ይልቅ ያንን አሉታዊ ኃይል ወደ ስራ በመለወጥ በሜዳ ላይ ባለው ውጤት ምላሽ ይሰጣል።
በንግድ ቀውስ፣ በፖሊሲ ውድቀት ወይም በገበያ ውድድር ወቅትም ውጤታማ መሪዎች ትችትንና ስህተትን እንደ ትምህርት ሊጠቀሙበት ይችላሉ።
የክርስቲያኖ ሮናልዶ የመሪነት ባህርይ በንግድ፣ በፖሊሲ አወጣጥ በቴክኖሎጂ እና በሌሎች ተቋማዊ መዋቅሮች ውስጥ ኃላፊነት ለሚወስዱ መሪዎች የሚሰጠው የፖሊሲ እና የስራ ትምህርት እጅግ የጎላ ነው።
ዕድሜው እየጨመረ ሲመጣ አቅሙን ከዕድሜው ጋር አጣጥሞ እስከ 40ዎቹ መጀመሪያ ድረስ በከፍተኛ ብቃት በውድድር ውስጥ መቆየት መቻሉ ገበያው፣ ቴክኖሎጂው እና የህዝብ ፍላጎት ቢቀየር እንኳን አዳዲስ የአሰራር መንገዶችን እየፈለጉ እስከመጨረሻው በጥንካሬ መቀጠል እንደሚገባ ያሳያል።
መሪዎች ድርጅታቸውን እና አሰራራቸውን ከዘመኑ ለውጥ ጋር በፍጥነት ማላመድ እና ራሳቸውን በየጊዜው ማደስ አለባቸው።
በሕይወትዎ የግል ዲሲፕሊንን በመጠበቅ ረገድ የሚገጥሙዎት ፈተናዎች ምንድን ናቸው?
ዛዲግ አብርሀ
የአፍሌክስ ፕሬዝደንት
#Ethiopia #GetuTemesgn
#Portugal #CristianoRonaldo
#Football #Ethics #workskills
Source: GetuTemesgen









No comments yet.