#FastMereja I በአዲስ አበባ ከተማ በመስክ የትራፊክ ደንብ ማስከበር ስራ ላይ በነበሩ የቁጥጥር ባለሙያዎች እና በአንድ አሽከርካሪ መካከል በተከሰተ አለመግባባትና ግጭት ምክንያት ሁለቱ የቁጥጥር ባለሙያዎች ለጊዜው ከስራ መታገዳቸውን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታወቀ።
በዛሬው እለት በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ሲሰራጭ የዋለውንና በቁጥጥር ባለሙያዎች እንዲሁም በአሽከርካሪው መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት የሚያሳይ ምስል ተከትሎ፣ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጉዳዩን ግራና ቀኝ በሚዛናዊነት በማጣራት ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል። የፍሬ ነገሩ ማጣራት ሂደት ተጠናቆ የመጨረሻ ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስም ሁለቱ ሰራተኞች ከስራ ታግደው እንዲቆዩ ተደርጓል።
ባለስልጣኑ አክሎ እንዳመለከተው፣ ማንኛውም አሽከርካሪ የትራፊክ ደንብ ተላልፎ ሲገኝ የመንጃ ፈቃድ ሲጠየቅ “አልሰጥም” በማለት የስራ እንቅፋት መፍጠር፣ ስድብና ዛቻ መሰንዘር እንዲሁም ሃይል በመጠቀም መደባደብ በህግ የሚያስጠይቅ ወንጀል ነው። ህብረተሰቡ የጉዳዩን ሂደት ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በኩል እንዲከታተልና በማህበራዊ ገጾች ከሚሰራጩ ያልተረጋገጡ መረጃዎች እንዲቆጠብ ጥሪ ቀርቧል።
Source: FastMereja









No comments yet.