በ8.6 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባው ቤት ለታዳጊ ካሊድ እና ለወንድሞቹ ተበረከተላቸው::
እናታቸውን ባጡበት ከባድ ቀን የ8ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተናውን በጽናት አጠናቆ ለብዙዎች መነቃቃትን የፈጠረው ታዳጊ ካሊድ ቃሲም እና ታናናሾቹ ተስፋ ተፈንጥቆላቸዋል።
በየካ ጣፎ «Muuxxannicha» ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ታዳጊ ካሊድ፣ እናቱ ከዚህ ዓለም በሞት በተለዩበት ዕለት “ምንም ዓይነት ችግር ቢገጥምህ ትምህርትህን እንዳታቋርጥ” የሚለውን የእናቱን የመጨረሻ ኑዛዜ በማስታወስ፣ የጠዋቱን ሁለት ፈተናዎች ተፈትኗል። በምሳ ሰዓት እረፍት ወደ ቤቱ ተመልሶ የእናቱን የቀብር ሥነ-ሥርዓት ያከናወነ ሲሆን፣ ከሰዓት በኋላም ወደ ፈተና ጣቢያው በመመለስ ቀሪውን ፈተና በጽናት አጠናቋል።
እናታቸው ከመለያየታቸው በፊት ከካሊድ በተጨማሪ ሁለት ትናንሽ ህፃናትን ጥለው ማለፋቸው ይታወቃል። አባታቸው በጅጅጋ ከተማ ሌላ ትዳር መስርተው በመኖራቸው፣ ካሊድ በታዳጊ ዕድሜው የሁለቱን ታናናሾቹን ኃላፊነት ለመሸከም ተገዶ ነበር።
በዚህም:
1. የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ሙሉ የቤት ውስጥ ቁሳቁስ ያሟላ ደረጃውን የጠበቀ አዲስ ቤት ከ 8.6 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ አስገንብቶ ለካሊድ እና ለታናናሾቹ አስረክቧል።
2. በአካባቢው ህብረተሰብ እና በበጎ ፈቃደኞች በተደረገ ጥረት 1.6 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቦ በካሊድ እና በወንድሞቹ የቁጠባ ደብተር ገቢ ሆኗል።
3. ለቤተሰቡ የሚያስፈልግ የምግብ እህል እና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።
በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ፣ የካሊድ ጽናት ለሁሉም ተማሪዎች አርአያ መሆኑን ገልጸው፣ ምንም አይነት ፈተና ቢገጥም ትምህርትን መቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።
@Seledadotio

No comments yet.