ማንኛውም አስመጪ ያስገባውን መኪና መሸጥ ያለበት ንግድ ፈቃድ ባወጣበት ቦታ ብቻ ነው።
የግብር ስወራ የፈጸሙ 7 የመኪና አስመጪዎች ላይ ዕርምጃ መውሰዱንም
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል
በመዲናዋ በመኪና አስመጪዎች እና በኮሚሽን ሠራተኞች በኩል የሚፈጸምን የታክስ ስወራ እና የግብር ማጭበርበር ድርጊት ለመግታት ጠንካራ የሕግ ማስከበር ሥራ እየሠራ መሆኑን ቢሮ አስታወቀ።
ቢሮው በሰጠው መግለጫ እንደገለጸው፣ በርካታ የመኪና አስመጪዎች ለከተማ አስተዳደሩ የሚገባውን ወርሃዊ ቫት እና ዓመታዊ ግብር ላለመክፈል ሲሉ ሽያጮቻቸውን በኮሚሽን ሠራተኞች አማካይነት እያካሄዱ ይገኛሉ።
በተጨማሪም አብዛኞቹ አስመጪዎች አድራሻቸው ሳይታወቅ ከዋጋ በታች ደረሰኝ በመቁረጥ ከፍተኛ የግብር ስወራ ወንጀል እንደሚፈጽሙ በተካሄደው ጥናት መረጋገጡ በመግለጫው ተጠቅሷል።
በታክስ ሕጉ መሠረት በሌሎች ክልሎች የተመዘገቡ አስመጪዎች አዲስ አበባ ውስጥ ሽያጭ ለማካሄድ በሚያስችል መልኩ የክልል ንግድ ፈቃዱን ማስጠቀስ፣ የመሸጫ ቦታ መከራየት እና የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽኖቻቸውን ማስተካከል ይጠበቅባቸዋል።
ማንኛውም አስመጪ ያስገባውን መኪና መሸጥ ያለበት በኮሚሽን ሠራተኞች አድራሻ ሳይሆን ንግድ ፈቃድ ባወጣበት ቦታ ብቻ ሊሆን እንደሚገባም ቢሮው አሳስቧል።
የኮሚሽን ንግድ ፈቃድ ያላቸው ሠራተኞችም ቢሆኑ በኮሚሽን ፈቃድ የመኪና መሸጫ ግቢዎችን ተከራይተው ከአስመጪዎች የተረከቧቸውን መኪኖች መሸጥ በሕግ ተጠያቂ የሚያደርግ የታክስ ስወራ ወንጀል መሆኑን ተገንዝበው ከድርጊቱ እንዲቆጠቡ ጥሪ ቀርቧል።
በተያያዘም ያገለገሉ መኪኖችን የሚሸጡ የኮሚሽን ኤጀንቶች ከአገለገሉ መኪኖች ውጪ አዲስ መኪና ሲሸጡ ከተገኙ በታክስ አስተዳደር አዋጁ መሠረት የቅጣት ዕርምጃ እንደሚወሰድባቸው ቢሮው አሳስቧል።
ኤጀንቶቹ ያገለገለ መኪና ሲሸጡም መረጃውን ለግብር ሰብሳቢው መሥሪያ ቤት በወቅቱ ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል ብለዋል
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.