ሐዋሳ ለሀይቅ ዳርቻ ልማት ድጋፍ ላደረጉ ባለሀብቶችና ተቋማት ጳጉሜን 5 የእውቅና መርሃ ግብር ልታዘጋጅ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የሐዋሳ ሀይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት በስኬት እንዲጀመር የገንዘብ ድጋፍ ላደረጉ ባለሀብቶች፣ ተቋማትና የልማት አጋሮች ጳጉሜን 5 ቀን 2018 ዓ.ም ታላቅ የእውቅናና የክብር መርሃ ግብር እንደሚካሄድ ተገለጸ።

ይህ የተገለጸው የሐዋሳ ሀይቅ ዳርቻ ልማት የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ የሐዋሳ እና የአዲስ አበባ አብይ ኮሚቴ አባላት በጋራ ባካሄዱት የምክክር መድረክ ላይ ነው።

በሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ጥራቱ በየነ በተመራው በዚህ መድረክ፤ ፕሮጀክቱ ለከተማዋ እድገት፣ ውበትና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ልዩ ትርጉም ያለው መሆኑ ተመልክቷል።

ከንቲባ ጥራቱ በየነ እንደገለጹት፤ ሐዋሳ ከተማ ላለፉት ዘጠኝ ወራት በከፍተኛ ፍጥነት በልማት ሃዲድ ላይ የምትገኝ ሲሆን፣ የሀይቅ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቱም የዚሁ ትልቅ ጥረት አካል ነው።

በመሆኑም ለዚህ ጥሪ ምላሽ በመስጠት ፕሮጀክቱን ለማስጀመር ገንዘብ ያበረከቱ የልማት ጀግኖችን ማመስገንና ማክበር አስፈላጊ በመሆኑ መርሃ ግብሩ መዘጋጀቱን አብራርተዋል።

የሚካሄደው የእውቅናና የምስጋና መድረክ፡

* ተሳታፊዎች: የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት ሥራ ሀላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው ባለሀብቶች እንዲሁም ሀገር አቀፍ ሚዲያዎች በተገኙበት በልዩ ድምቀት ይከናወናል።

* የተሳታፊዎች መስፈርት: የክብር እውቅናው የሚሰጠው ለልማቱ ለመደገፍ ቃል የገቡትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ገቢ ላደረጉ አካላት ብቻ እንደሆነ ተጠቁሟል።

የሐዋሳ ከተማ ኮሙኒኬሽን እንደገለጸው፤ ይህ መርሃ ግብር ከተማዋ ለልማት አጋሮቿ ያላትን አክብሮት የሚያሳይና በቀጣይም ተመሳሳይ የማህበረሰብና የኢኮኖሚ ልማቶችን ለማፋጠን መንገድ የሚከፍት ነው።






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2