በአዲስ አበባ ታገታ የተወሰደች ህፃንን ለማስለቀቅ ሶስት ሚሊዮን ብር የጠየቀች የቤት ሰራተኛ በጎንደር ከተማ በቁጥጥር ስር ዋለች
#Ethiopia | በአዲስ አበባ ከተማ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ከምትሰራበት መኖሪያ ቤት የሰባት ዓመቷን ህፃን ፊዮና ሰለሞንን በማገት ወደ ጎንደር ከተማ በመውሰድ ከቤተሰቦቿ ገንዘብ ለመቀበል የሞከረችው ወጣት መቅደስ ሞገስ በቁጥጥር ስር መዋሏን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
የመምሪያው አዛዥ ኮማንደር አንተነህ ቴዎድሮስ እንደገለጹት ተጠርጣሪዋ ህፃኗን አግታ ወደ ጎንደር ካመጣች በኋላ በከተማዋ ማራኪ ክፍለ ከተማ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ በሚገኝ ጫካ ውስጥ ደብቃ በነበረበት ወቅት በህብረተሰቡ ጥቆማና በፖሊስ በተደረገ ጥብቅ ክትትል ልትያዝ ችላለች።
ተጠርጣሪዋ ለጊዜው ካልተያዘው ግርማ ወንድአሁን ከተባለ የአክስቷ ልጅ ጋር በመተባበር ወንጀሉን የፈፀመች ሲሆን ለህፃኗ ቤተሰቦች ስልክ በመደወል ሶስት ሚሊዮን ብር የጠየቁ ቢሆንም ከሶስት መቶ ሰባ ሺህ ብር በላይ ተቀብለው መገኘታቸውን ኮማንደሩ አብራርተዋል።
ፖሊስ ከአደጋው ያመለከተውን ግብረ አበር ጨምሮ ከጉዳዩ ጋር እጃቸው ያለበትን ሌሎች አካላት በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥብቅ ክትትል በማድረግ ላይ ይገኛል።
#Gondar #AddisAbaba #EthiopianPolice #CrimeNews #Ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Source: GetuTemesgen








No comments yet.