#FastMereja | በ2026 በሚካሄደው 73ኛው የሚስ ወርልድ ምርጥ ውዝዋዜዎች ዘርፍ የኢትዮጵያ ተወካይ አንደኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።
እንደ ቢፔጀንት ኮርነር ይፋዊ ደረጃ አሰጣጥ መረጃ፣ የኢትዮጵያ ተወካይ ውበትንና ባህላዊ እሴትን በተላበሰ ድንቅ የውዝዋዜ ብቃት የመጀመሪያውን ደረጃ በመያዝ የቀደመች ሲሆን፣ ማሌዢያ እና ህንድ በቅደም ተከተል ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃን ይዘዋል። ፍሬንች ጊያና እና ዶሚኒካን ሪፐብሊክ ደግሞ በምርጥ አምስቱ ውስጥ ተካተዋል።
በዚሁ ዝርዝር ውስጥ
🇳🇿 ኩክ አይላንድስ
🇫🇷 ፈረንሳይ
🇧🇷 ብራዚል
🇧🇴 ቦሊቪያ
🇻🇳 ቬትናም
🇱🇦 ላኦስ
🇮🇩 ኢንዶኔዢያ
🇬🇶 ኢኳቶሪያል ጊኒ
🇨🇱 ቺሊ
🇵🇱 ፖላንድ
🇧🇪 ቤልጂየም
🇪🇸 ስፔን
🇹🇭 ታይላንድ
🇳🇵 ኔፓል
🇱🇰 ስሪላንካ የተወከሉ ተወዳዳሪዎች በምርጥ 20 ተወዳዳሪዎች ዝርዝር ውስጥ መካተት ችለዋል።
የውድድሩ የዳኝነት አካላት የኢትዮጵያ ተወዳዳሪ ያቀረበችውን ድንቅ የባህል እንቅስቃሴ፣ አልባሳት እና አጠቃላይ የውዝዋዜ ክህሎት ከፍተኛ ነጥብ በመስጠት እንዳደነቁት ተነግሯል።
Source: FastMereja








No comments yet.