#FastMereja I ኦርቢክስ ቴክኖሎጂስ ኃ. የተ. የግ. ማህበር የተሰኘ የሀገር ውስጥ የቴክኖሎጂ ስታርትአፕ፣ ፓርኪንግን፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን፣ የህዝብ ጥቆማዎችን እና የቱሪዝም መዳረሻዎችን በአንድ ላይ የሚያገናኝ ኦርቢክስ (Orbix) የተሰኘ የተቀናጀ ዲጂታል ፕላትፎርም ይፋ ማድረጉን አስታወቀ።
ድርጅቱ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይህ ፕላትፎርም በተበታተነ መልኩ የሚሰጡ የከተማ አገልግሎቶችን በአንድ ስነ-ምህዳር ስር በማምጣት የሀገሪቱን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማገዝ ያለመ ነው።
ኦርቢክስ አራት ዋና ዋና አገልግሎቶችን የያዘ ሲሆን፣ የመጀመሪያው የስማርት ፓርኪንግ አገልግሎት አሽከርካሪዎች የፓርኪንግ ቦታዎችን በዲጂታል መንገድ እንዲፈልጉ፣ እንዲይዙ እና ክፍያ እንዲፈፅሙ ያመቻቻል። ሁለተኛው የኦርቢክስ ኢቪ አገልግሎት ደግሞ በኢትዮጵያ እየተስፋፋ ያለውን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ለመደገፍ፣ የቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎችን መፈለጊያ፣ ቦታ መያዣ እና ዲጂታል ክፍያ መፈፀሚያ አገልግሎት ይሰጣል።
በሦስተኛ ደረጃ የተቀመጠው አይሀብ (iHub) የህዝብ ጥቆማ እና ተሳትፎ ፕላትፎርም ሲሆን፣ ዜጎች የመንገድ ብልሽቶችን፣ የትራፊክ አደጋዎችን እና የህዝብ አገልግሎት እክሎችን በፎቶ እና ቪዲዮ አስደግፈው ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጥቆማ የሚያደርሱበት ነው። አራተኛው ኢትዮ ፓርክስ ደግሞ የሀገሪቱን የቱሪዝም መዳረሻዎች፣ ፓርኮች እና የመዝናኛ ቦታዎች በዲጂታል መንገድ ለማስተዋወቅና አገልግሎቶችን ለማቀናጀት የተዘረጋ ነው ተብሏል።
#ሳይ_ቴክ



Source: FastMereja








No comments yet.