የናሚቢያ የሥራ እና ትራንስፖርት ሚኒስቴር አዲስ ብሔራዊ አየር መንገድን እንደገና ለማቋቋም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ስትራቴጂካዊና ቴክኒካዊ ውይይቶች እየተደረጉ መሆኑን አስታወቀ። ይህ መግለጫ የወጣው በሁለቱ አካላት ትብብር ላይ የውጭ ቁጥጥር ይኖረዋል የሚሉ ስጋቶች በብዙኃን መገናኛዎች ከተንጸባረቁ በኋላ ነው።
የሚኒስቴሩ ዋና ኃላፊ ዮናስ ሺሎንጎ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ከአገር ውስጥ አቪዬሽን ባለሙያዎች ጋር የሚደረጉ ውይይቶች ገና በቅድመ-ዝግጅት ደረጃ ላይ ያሉና ምንም ዓይነት ስምምነት ያልተደረገባቸው መሆናቸውን አስገንዝበዋል። የዚህ ጥረት ዋና ዓላማ የናሚቢያን ብሔራዊ ጥቅሞችና ባለሙያዎች ያማከለ ጠንካራ አየር መንገድ መዘርጋት እንደሆነ ገልጸዋል።
Via capital
Source: Yeneta Tube









No comments yet.