#FastMereja I በአዲስ አበባ ከተማ ተቀጥራ ከምትሰራበት ቤት የ7 ዓመት ህፃንን በማ ገት 3 ሚሊዮን ብር የጠየቀችው የቤት ሰራተኛ፣ በጎንደር ከተማ በተደረገ የፖሊስ ክትትልና የህዝብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሏን የጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።
እገ ታውን የፈጸመችው ወጣት መቅደስ ሞገስ የተባለች የቤት ሰራተኛ ህፃን ፊዮና ሰለሞንን ከአዲስ አበባ አ ግታ ወደ አማራ ክልል ጎንደር ከተማ በመውሰድ በቁጥጥር ስር መዋሏን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር አንተነህ ቴዎድሮስ ገልጸዋል።
እንደ ኮማንደሩ ማብራሪያ፣ ተጠርጣሪዋ ህፃኗን በከተማዋ ማራኪ ክፍለ ከተማ ዩኒቨርሲቲ አቅራቢያ በሚገኝ ጫካ ውስጥ ደብቃ የነበረ ቢሆንም፣ በተደረገበት ብርቱ ክትትልና ከህዝብ በተገኘ ጥቆማ ህፃኗን በሰላም ማዳን ተችሏል።
ተጠርጣሪዋ ወንጀሉን ካልተያዘው ግርማ ወንድአሁን ከተባለ የአክስቷ ልጅ ጋር በመቀናጀት የፈጸመችው ሲሆን፣ ለህፃኗ ቤተሰቦች ስልክ በመደወል 3 ሚሊዮን ብር በመጠየቅ ከ370 ሺህ ብር በላይ ተቀብለው እንደነበር ተረጋግጧል።
ፖሊስ ከተያዘችው የቤት ሰራተኛ በተጨማሪ ከወንጀሉ ጋር አብረው የተሳተፉ ሌሎች ተጠርጣሪዎችንና አጋሮችን በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥብቅ ክትትል ማድረጉን ቀጥሏል።
Source: FastMereja








No comments yet.