#Ethiopia | የኢትዮጵያን የቤት አቅርቦት ፍላጎት ለማሟላትና የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ባለቤት የመሆን ህልም ለማቃለል ያለመ ግዙፍ የሪል እስቴት ኤክስፖ ተዘጋጀ።
የአርኪ ኢቨንት ኦርጋናይዘር ባለቤት አቶ ዮሃንስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት፣ 6ኛው “Arki Homes Expo” “በአዲስ ዓመት አዲስ ቤት” በሚል መሪ ቃል ከመስከረም 8 እስከ 10 ቀን 2019 ዓ.ም በጊዮን ሆቴል በደመቀ ሁኔታ ይካሄዳል።
ይህ ኤክስፖ በተለይም ለአዲስ ዓመትና መስቀል በዓላት ወደ ሀገራቸው የሚገቡ የዲያስፖራ አባላትን እንዲሁም በአዲሱ ዓመት የቤት ባለቤት የመሆን እቅድ ያላቸውን ሀገር ውስጥ የሚኖሩ ገዢዎችን ማዕከል ያደረገ ነው።
በኤክስፖው ላይ በከተማችን በታማኝነታቸው፣ በግንባታ ጥራታቸውና በፍጥነታቸው የሚታወቁ ከ20 በላይ አጋር የሪል እስቴት አልሚዎች የሚሳተፉ ሲሆን ምርቶቻቸውንና የበዓል ቅናሾቻቸውን ይዘው ይቀርባሉ።
ኤክስፖው ገዢዎችና አልሚዎች በቀጥታ የሚገናኙበት መድረክ ከመሆኑ ባሻገር ቤተሰብ ከልጆቹ ጋር መጥቶ እየተዝናና የሚገበያይበት ሰፊ ቦታና የመዝናኛ ፕሮግራሞች ተዘጋጅተዋል።
አዘጋጆቹ መላው የህብረተሰብ ክፍልና የቤት ፈላጊዎች በጊዮን ሆቴል በመገኘት በግልጽ መረጃ ላይ የተመሰረተ የቤት ውሳኔ እንዲያደርጉና አዲሱን ዓመት በራሳቸው ቤት እንዲቀበሉ ጥሪ አቅርበዋል።
📸 ከበደ መክብብ
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu



Source: GetuTemesgen








No comments yet.