የአሜሪካ የግምጃ ቤት የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምስል ያረፈበትን አዲስ የ1 ዶላር ሳንቲም ይፋ አደረገ፡፡የአሜሪካ የግምጃ ቤ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የአሜሪካ የግምጃ ቤት የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምስል ያረፈበትን አዲስ የ1 ዶላር ሳንቲም ይፋ አደረገ፡፡
የአሜሪካ የግምጃ ቤት መሥሪያ ቤት የሀገሪቱን የ250ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምስል ያረፈበትን አዲስ የ1 ዶላር ሳንቲም ይፋ አደረገ።
ይሁን እንጂ የዚህ ሳንቲም መታተም በሕይወት ያሉ ፕሬዝዳንቶች ምስል በሀገሪቱ ገንዘብ ላይ እንዳይሰፍር የሚከለክለውን የፌደራል ሕግ የሚቃረን በመሆኑ ከፍተኛ አነጋገር ፈጥሯል።
ሳንቲሞቹ የተዘጋጁት ዩናይትድ ስቴትስ የ250ኛ ዓመት የምስረታ በዓሏን የምታከብርበትን ዓመተ ምህረት (1776-2026) ለማስታወስ ነው።
25 ሳንቲሞችን የያዘ ጥቅል በ61 ዶላር (144 በመቶ የዋጋ ጭማሪ ያለው) ሲሸጥ፣ 100 ሳንቲሞች ያሉት ከረጢት ደግሞ በ154.50 ዶላር ለገበያ ቀርቧል።
የአሜሪካ የሳንቲም ማዕከል ሳንቲሞቹ በገበያ ላይ ለዝውውር ጭምር የሚያገለግሉ መሆናቸውን ያረጋገጠ ሲሆን፣ ይህ ድርጊት በሕይወት ያለ ፕሬዝዳንት በገንዘብ ላይ ሊቀረጽ አይችልም የሚለውን ነባር የፌደራል ሕግ በቀጥታ የሚጥስ ነው። ሳንቲሙ
በአንዱ በኩል የትራምፕ ምስል፣ “ነጻነት”፣ “በእግዚአብሔር እናመናለን” የሚሉ ቃላት እና የ1776-2026 ዓመተ ምህረት ያረፈበት ሲሆን፣ በሌላኛው ገጹ ደግሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ማህተምን ይዟል።
ባለፈው ግንቦት ወር የፋይናንስ ሚኒስትሩ ስኮት ቤሰንት የትራምፕ ምስል ያለበት የ250 ዶላር የብር ኖት ለማውጣት እቅድ መኖሩን መናገራቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ባለፈው መጋቢት ወር ደግሞ የትራምፕ ፊርማ በአሜሪካ የብር ኖቶች ላይ ማረፍ መጀመሩ ተገልጿል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: