የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 63 ታራሚዎች ውስጥ 62 የህግ ታራሚዎች ሙሉ በሙሉ ማለፋቸው ተነገረ።የ12 ክፍል ማለፊያ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 63 ታራሚዎች ውስጥ 62 የህግ ታራሚዎች ሙሉ በሙሉ ማለፋቸው ተነገረ።
የ12 ክፍል ማለፊያ ነጥብ ካመጡት ውስጥ 7ቱ ሴት ታራሚዎች ይገኙበታልም ተብላል፡፡

 
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በከፍተኛ ጥበቃና በሴቶች ማረሚያና ማረፊያ ማዕከል እና በዘዋይ ማረሚያ ማእከላት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱት ተፈታኞች 63 ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ 62 ማለፋቸውን ማረመያ ቤቱ አስታውቋል፡፡
 
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ማዕከል ፣ በሴቶች ማረሚያ ማዕከላት በመደበኛ የትምህርት መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ እና ለፈተና የተቀመጡት 31 የህግ ታራሚዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችለውን ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል፤ከነዚህም ውስጥ 7ቱ ሴቶች መሆናቸው ታውቋል፡፡
 
በተመሳሳይ የዝዋይ ማረሚያ ማዕከል ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ካስፈተናቸው 23 የህግ ተማሪዎች  መካከል 22ቱን ማሳለፍ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን በአጠቃላይ በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ፈተና ከወሰዱ 63 ታራሚስች 62 ማለፋችው ተነግራል፡፡የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ካስፈተናቸው በሁለቱ ማዕከላት አጠቃላይ ተፈታኝ ተማሪዎች መቶ በመቶ ወደ ዩኒቨርስቲ መግባት የሚያስችላቸውን ውጤት ማስመዘገብ ተችሏል፡፡
የሕግ ታራሚ ተማሪዎች ያስመዘገቡትን ውጤት ተከትሎ የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል የመጀመሪያ ደረጃና አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ሳምሶን ወንድሜነህ እንደተናገሩት ማረሚያ ቤቱ ለታራሚዎች የፈጠረው ምቹ የትምህርት ከባቢ እና የታሪሚዎች ጠንካራ ተነሳሽነት ለዚህ አስደናቂ 100 ከመቶ ውጤት ዋነኛ ምክንያቶች መሆናቸውን ተናግረዋል።
በማዕከላቱ የሚገኙት ትምህርት ቤቶች እንደማንኛውም የህዝብ ት/ቤት ደረጃውን የጠበቀና የተሟላ መምህራን የተመደቡለት መሆኑን የገለፁት አቶ ሳምሶን የህግ ታራሚ ተማሪዎችም በህግ ጥላ ስር ቢሆኑም ትምህርታቸውን በአግባቡ ሲከታተሉ መቆየታቸውንና ለውጤት እንደበቁም አመላክተዋል፡፡
አቶ ሳምሶን አክለውም በማረሚያ ቤት ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ታራሚዎች ተስፋና መነሳሳትን የፈጠረ ሲሆን ማረሚያ ቤት የህይወት ማብቂያ ሳይሆን አዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ መሆኑን በተግባር ያሳየ ነው፤ ብለዋል።
የህግ ታራሚ ተማሪዎች  ያመጡት ውጤት መታረምና መታነፃቸውን ማሳያ በመሆኑን ገልፀው መንግስት በይቅርታና ምህረት መልቀቅ የሚችልበትን መንገድ አሊያም የትምህርት ሚኒስቴር የሕግ ታራሚ መሆናቸውን በመረዳት ትምህርታቸውን በርቀት እንዲከታተሉ ዩኒቨርሲቲዎችን
እንዲያመቻችላቸው ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
 
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2