ፕሬዚዳንት ሩቶ አምባሳደር ባጫ ደበሌን ተሰናበቱ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ አገልግሎታቸውን ላጠናቀቁት በኬንያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ጀነራል ባጫ ደበሌ በናይሮቢ በሚገኘው የፕሬዚዳንት ቤተ መንግስት ሽኝት አደረጉላቸው።

ፕሬዚዳንቱ በስንብት ስነ-ስርዓቱ ወቅት ለአምባሳደሩ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበው ወደፊት በሚያካሂዷቸው የስራ እንቅስቃሴዎች ሁሉ ስኬትና መልካም እድል ተመኝተውላቸዋል።

​በሽኝት ስነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዚዳንት ሩቶ በኢትዮጵያና በኬንያ መካከል ያለው የወዳጅነት የህዝብ ለህዝብና የሁለቱ መንግስታት መሪዎች ግንኙነት እጅግ በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

አክለውም ይህ ዘለቄታዊ ወዳጅነትና አጋርነት በተለይም ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እየጠናከረና እያደገ መምጣቱን በጥብቅ አስረድተዋል።

​ሁለቱ ሀገራት በቀጣይም ቢሆን በትብብር የሚሰሯቸውን ዘርፈ ብዙ ስራዎች አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የገለጹት ፕሬዚዳንቱ በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ያለውን ግንኙነት ማሳደግ፣ በጋራ ወሰኖች አካባቢ አስተማማኝ ደህንነትንና ሰላምን ማስፈን እንዲሁም በዜጎች መካከል ያለውን የህዝብ ለህዝብ ትስስር ይበልጥ ማጠናከር ቀዳሚ ትኩረታቸው እንደሚሆን አረጋግጠዋል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1