#Ethiopia | የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ፀሐፊ የሆኑት መጋቢ ጌትነት ለማ ከማንኛውም የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እና ውክልና በጊዜያዊነት እንዲታገዱ ተወሰነ።
የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ዋና ጽሕፈት ቤት ባወጣው ይፋዊ ደብዳቤ እንዳስታወቀው፣ ውሳኔው የተላለፈው በመጋቢ ጌትነት ለማ የሕይወትና የአገልግሎት ንጽህና ዙሪያ በማህበራዊ ሚዲያዎችና በወንጌላውያን ምዕመናን መካከል ሲሰራጩ የነበሩ አሉታዊ ዘገባዎችንና መረጃዎችን በተረጋጋ ሁኔታ ለማጣራት እንዲቻል ነው።
ቤተ ክርስቲያኗ ቀደም ሲል ከመጋቢ ጌትነት ጋር በጉዳዩ ላይ ምክክር አድርጋ እንደነበር የገለጸች ሲሆን ለተነሱት ነጥቦች ትክክለኛነት ተጣርተው አጠቃላይ ማብራሪያ ለሥራ አስፈጻሚ ቦርድ እስከሚቀርብ ድረስ እገዳው እንደሚቀጥል አስታውቃለች።
የቤተ ክርስቲያኗ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ በጸደቀው ውሳኔ መሠረት መጋቢጌትነት ደብዳቤው ከተጻፈበት ከዛሬ ጀምሮ ከማንኛውም የቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎትና ውክልና ታግደው እንዲቆዩ ተደርጓል።
ይህ የምርመራ ጊዜ መጋቢ ጌትነትም ሆኑ ቤተሰባቸው ከእግዚአብሔር ጋር የሚያሳልፉት የመታደስ ጊዜ እንደሚሆንላቸው ተስፋ እንደሚያደርግ የገለጸው የቤተ ክርስቲያኗ ዋና ጽሕፈት ቤት ምዕመናንም በጸሎትና በምክር ከጎናቸው እንዲቆሙ ጥሪ አቅርቧል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.